Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 23:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት አገ​ል​ግ​ሎት በሠሩ ከሃያ አም​ስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነ​በሩ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በስ​ማ​ቸው በተ​ቈ​ጠ​ሩት ላይ የአ​ባ​ቶች ቤት አለ​ቆች የሆ​ኑት በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነ​ዚህ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እንግዲህ እነዚህ የቤተ ሰቡ አለቆች ሆነው እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተመዝግበው የተቈጠሩት የሌዊ ዘሮች ናቸው፤ ዕድሜያቸውም ሃያና ከዚያ በላይ የሆናቸው በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የጌታን ቤት አገልግሎት በሠሩ ዕድሜአቸው ሀያ ዓመትና ከዚያም ላይ በነበሩ በእያንዳንዳቸው በስማቸው በተቆጠሩት ላይ የአባቶች ቤት አለቆች የሆኑት በየአባቶቻቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነዚህ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እንግዲህ እነዚህ ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተሰባቸው የተዘረዘሩት የሌዊ ዘሮች ሲሆኑ፥ እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተጠቅሰዋል። ኻያ ዓመት የሞላው ወይም ከዚያ በላይ የሆነው እያንዳንዱ የሌዊ ዘር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ባለው ሥራ ድርሻ ነበረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የእግዚአብሔርን ቤት አገልግሎት በሠሩ ከሃያ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ በነበሩ በእያንዳንዳቸው በስማቸው በተቈጠሩት ላይ የአባቶች ቤት አለቆች የሆኑት በየአባቶቻቸው ቤት የሌዊ ልጆች እነዚህ ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 23:24
20 Referencias Cruzadas  

የሐ​ሙሲ ልጆች፤ ሞዓሊ፥ አዴር፥ ኢያ​ሪ​ሞት ሦስት ነበሩ።


በመ​ጨ​ረ​ሻ​ውም በዳ​ዊት ትእ​ዛዝ ከሃያ አም​ስት ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት የሌዊ ልጆች ተቈ​ጠሩ።


ሌዋ​ው​ያ​ንም ከሠ​ላሳ ዓመት ዕድሜ ጀምሮ ወደ ላይ ተቈ​ጠሩ፤ ቍጥ​ራ​ቸ​ውም በእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ ነፍስ ወከፍ ሲቈ​ጠሩ ሠላሳ ስም​ንት ሺህ ነበረ።


በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤት ለተ​ቈ​ጠሩ ካህ​ናት፥ ከሃያ ዓመ​ትም ወደ ላይ ላሉ በየ​ሥ​ር​ዐ​ታ​ቸ​ውና በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው ለተ​ቈ​ጠሩ ሌዋ​ው​ያን፥


በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወዳ​ለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በመጡ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር የሰ​ላ​ት​ያል ልጅ ዘሩ​ባ​ቤል፥ የኢ​ዮ​ሴ​ዴ​ቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀ​ሩ​ትም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን፥ ከም​ርኮ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የተ​መ​ለ​ሱት ሁሉ ጀመሩ፤ ሌዋ​ው​ያ​ን​ንም ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ሥራ እን​ዲ​ያ​ሠ​ሩት ሾሙ​አ​ቸው።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ቅጥሩ ከተ​ሠራ በኋላ፥ ሳን​ቃ​ዎ​ቹን አቆ​ምሁ፤ በረ​ኞ​ቹ​ንና መዘ​ም​ራ​ኑን፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም ሾምሁ፤


በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ማኅ​በ​ሩን ሁሉ ሰበ​ሰ​ቡ​አ​ቸው፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ወንድ ሁሉ በየ​ራሱ፥ በየ​ወ​ገ​ኑም፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች፥ በየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ተና​ገሩ።


የስ​ም​ዖን ልጆች በየ​ት​ው​ል​ዳ​ቸው፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች የተ​ቈ​ጠሩ፥ እንደ እየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር፥ በየ​ራ​ሳ​ቸው ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለው ወንድ ሁሉ፥ ወደ ሰልፍ የሚ​ወ​ጡት ሁሉ፥


ድን​ኳ​ኑም ተነ​ቀለ፤ ድን​ኳ​ኑ​ንም የተ​ሸ​ከሙ የጌ​ድ​ሶን ልጆ​ችና የሜ​ራሪ ልጆች ተጓዙ።


የቀ​ዓ​ትም ልጆች ንዋየ ቅድ​ሳ​ቱን ተሸ​ክ​መው ተጓዙ፤ እነ​ዚ​ህም እስ​ኪ​መጡ ድረስ እነ​ዚያ ድን​ኳ​ኑን ተከሉ።


እንደ ገና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ቍጣ እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው እና​ንተ የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንና የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ሕግ ጠብቁ።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች የተ​ቈ​ጠሩ እነ​ዚህ ናቸው፤ ከየ​ሰ​ፈሩ በየ​ሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው የተ​ቈ​ጠሩ ሁሉ ስድ​ስት መቶ ሦስት ሺህ አም​ስት መቶ አምሳ ነበሩ።


“የሌ​ዊን ልጆች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች፥ በየ​ወ​ገ​ና​ቸ​ውም ቍጠር፤ ወን​ዱን ሁሉ ከአ​ንድ ወር ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ቍጠ​ራ​ቸው።”


የሜ​ራ​ሪም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ሞሐሊ፥ ሙሲ። የሌ​ዋ​ው​ያን ወገ​ኖች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እነ​ዚህ ናቸው።


በየ​ራሱ አም​ስት ዲድ​ር​ክም ውሰድ፤ እንደ መቅ​ደሱ ዲድ​ር​ክም ብዛት ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ ዲድ​ር​ክም ሃያ አቦሊ ነው።


የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠ​ራ​ቸው።


ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​በ​ትን ሁሉ ትለ​ያ​ለህ።


“የሌ​ዋ​ው​ያን ሕግ ይህ ነው፤ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያሉት እስከ አምሳ ዓመት ድረስ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ይገ​ባሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos