ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢበኖብ የተባለ ዳዊትን ለመግደል አሰበ። የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ።
1 ዜና መዋዕል 20:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚያም በጌት ውስጥ ከራፋይም የተወለዱ ነበሩ፤ በዳዊትም እጅ በባርያዎቹም እጅ ወደቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጋት የነበሩ የራፋይም ዘሮች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም በዳዊትና በሰዎቹ እጅ ወደቁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዳዊትና በሠራዊቱ የተገደሉት እነዚህ ሦስቱ ሰዎች ኀያላን ከሆኑት የራፋይም ዘር ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህም በጌት ውስጥ ከኀያላን የተወለዱ ነበሩ፤ እነርሱም አራት ኀያላን ነበሩ፤ በዳዊትም እጅ በአገልጋዮቹም እጅ ወደቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚያም በጌት ውስጥ ከራፋይም የተወለዱ ነበሩ፤ በዳዊትና በባሪያዎቹ እጅ ወደቁ። |
ከራፋይም ዘሮች አንዱ የሆነ ይሽቢበኖብ የተባለ ዳዊትን ለመግደል አሰበ። የናስ ጦሩ ሦስት መቶ ሰቅል የሚመዝንና አዲስ ሰይፍ የታጠቀ ሰው ነበረ።
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሐይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ፍልምያ ለኃያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ሀብትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለአዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፥ ጊዜና እድል ግን ሁሉን ይገናኛቸዋል።
አሁን እንግዲህ በዚያን ቀን ጌታ የተናገረውን ይህን ተራራማ አገር ስጠኝ፤ አንተ በዚያ ቀን ዔናቃውያን ታላላቆችና የተመሸጉ ከተሞችም በዚያ እንዳሉ ሰምተህ ነበር፤ ምናልባት ጌታ ከእኔ ጋር ይሆናል፥ ጌታም እንደ ተናገረኝ አሳድዳቸዋለሁ።”