ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ተቆዓ ሰው ልኮ አንዲት ብልኅ የሆነች ሴት አስመጣ፤ እንዲህም አላት፤ “ኀዘንተኛ በመምሰል የኀዘን ልብስ ልበሺ፤ ዘይት አትቀቢ፤ ለሞተ ሰው ብዙ ጊዜ እንዳዘነች ሴት ትሆኛለሽ፤
1 ዜና መዋዕል 2:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤስሮምም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮም ሚስት አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤስሮም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ፣ ሚስቱ አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሔጽሮን በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ ሚስቱ አብያ አሽሑር የተባለውን ልጁን ወለደችለት አሽሑርም የተቆዓ አባት ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤስሮምም ከሞተ በኋላ ካሌብ ወደ ኤፍራታ መጣ። የኤስሮምም ሚስት አብያ የቴቁሔን አባት አስሖርን ወለደችለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤስሮምም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮም ሚስት አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት። |
ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ተቆዓ ሰው ልኮ አንዲት ብልኅ የሆነች ሴት አስመጣ፤ እንዲህም አላት፤ “ኀዘንተኛ በመምሰል የኀዘን ልብስ ልበሺ፤ ዘይት አትቀቢ፤ ለሞተ ሰው ብዙ ጊዜ እንዳዘነች ሴት ትሆኛለሽ፤
ጌሹርና አራምም የኢያዕርን ከተሞች ከቄናትና ከመንደሮችዋ ጋር ስልሳውን ከተሞች ወሰዱባቸው። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ልጆች ነበሩ።
የአሞጽ ቃላት፥ በቴቁሔ ከሚገኙ ከበግ አርቢዎች መካከል የነበረ፥ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ዘመን፥ በእስራኤልም ንጉሥ በዮአስ ልጅ በኢዮርብዓም ዘመን፥ የምድር መናወጥ ከመሆኑ ከሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል ያየው ይህ ነው።