Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 2:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከሔጽሮን በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ ሚስቱ አብያ አሽሑር የተባለውን ልጁን ወለደችለት አሽሑርም የተቆዓ አባት ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ኤስሮም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ፣ ሚስቱ አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ኤስሮምም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮም ሚስት አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ኤስ​ሮ​ምም ከሞተ በኋላ ካሌብ ወደ ኤፍ​ራታ መጣ። የኤ​ስ​ሮ​ምም ሚስት አብያ የቴ​ቁ​ሔን አባት አስ​ሖ​ርን ወለ​ደ​ች​ለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ኤስሮምም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮም ሚስት አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 2:24
8 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም በተቆዓ የምትኖረውን አንዲት ብልኅ ሴት አስጠራ፤ እርስዋም በደረሰች ጊዜ “ሐዘንተኛ ለመምሰል ሞክሪ፤ የሐዘን ልብስሽን ልበሺ፤ ቅቤም አትቀቢ፤ ለብዙ ጊዜ በሐዘን ላይ የቈየሽ ሴት ለመምሰል ተዘጋጂ፤


ነገር ግን የገሹርና የአራም ነገሥታት ሥልሳ የሚያኽሉ ታናናሽ ከተሞችን ከዚያው ከገለዓድ ድል አድርጎ ያዘ፤ ይህም የያኢርንና የቀናትን መንደሮች እንዲሁም በአቅራቢያቸው ያሉትንም ታናናሽ ከተሞች የሚያጠቃልል ነበር፤ በዚያ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ናቸው፤


የሔጽሮን የበኲር ልጅ ይራሕመኤል አምስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም የመጀመሪያው ራም ቀጥሎም ቡና፥ ኦሬን፥ ኦጼምና አሒያ ተብለው የሚጠሩ ነበሩ፤


ሔጽሮን ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ይራሕመኤል፥ ራምና ካሌብ ተብለው የሚጠሩ ናቸው፤


የተቆዓን ከተማ የቈረቈረው አሽሑር፥ ሔላና ናዕራ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ሚስቶች ነበሩት፤


ዖዝያን በይሁዳ፥ የዮአስ ልጅ ኢዮርብዓምም በእስራኤል ላይ በነገሡበት ዘመን፥ በተቆዓ ከሚገኙ እረኞች አንዱ የሆነው አሞጽ የምድር መናወጥ ከመሆኑ ሁለት ዓመት በፊት ስለ እስራኤል የተናገረው የትንቢት ቃል ይህ ነው።


ይህም ከመሆኑ በፊት በይሁዳ ደቡብ የምትገኘውን የከሪታውያንን ግዛትና የካሌብን ግዛት በመውረር ጺቅላግን አቃጥለናታል” ሲል መለሰለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos