1 ዜና መዋዕል 19:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህም በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ ሞተ፥ ልጁም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ ሞተ፤ ልጁም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጥቂት ጊዜ በኋላ የዐሞን ንጉሥ ናዖስ ሞተ፤ በእርሱም እግር ተተክቶ ልጁ ሐኑን ነገሠ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የአሞን ልጆች ንጉሥ ናዖስ ሞተ፤ ልጁም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም በኋላ የአሞን ልጆች ንጉሥ ናዖስ ሞተ፤ ልጁም በእርሱ ፋንታ ነገሠ። |
ዳዊትም፦ “አባቱ ስላደረገልኝ ወረታ እኔ ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነት አደርጋለሁ” አለ። ዳዊትም አባቱ ስለ ሞተ ሊያጽናናው መልእክተኞችን ላከ፤ የዳዊትም ባርያዎች ሊያጽናኑት ወደ ሐኖን ወደ አሞን ልጆች ምድር መጡ።
የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ እንደመጣባችሁ ባያችሁ ጊዜ ግን፥ አምላካችሁ ጌታ ንጉሣችሁ ቢሆንም እንኳን፥ ‘አይሆንም፤ የሚገዛን ንጉሥ እንፈልጋለን’ አላችሁ።