Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 19:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዳዊትም፦ “አባቱ ስላደረገልኝ ወረታ እኔ ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነት አደርጋለሁ” አለ። ዳዊትም አባቱ ስለ ሞተ ሊያጽናናው መልእክተኞችን ላከ፤ የዳዊትም ባርያዎች ሊያጽናኑት ወደ ሐኖን ወደ አሞን ልጆች ምድር መጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ዳዊትም፣ “አባቱ ለእኔ በጎ ነገር እንዳደረገልኝ እስኪ እኔም ለናዖስ ልጅ ለሐኖን በጎ ነገር ላድርግለት” ብሎ ዐሰበ። ስለዚህ ዳዊት ስለ አባቱ ሞት ሐዘኑን ለመግለጽ ወደ ሐኖን መልክተኞችን ላከ። የዳዊት ሰዎች ሐዘናቸውን ለመግለጽ ሐኖን ወደሚኖርበት ወደ አሞናውያን ምድር በመጡ ጊዜ፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ንጉሥ ዳዊትም “አባቱ ናዖስ ለእኔ እንዳደረገልኝ ሁሉ፥ እኔም ለልጁ ለሐኑን ታማኝ ወዳጅ በመሆን ወሮታውን እከፍላለሁ” አለ፤ ስለዚህም ዳዊት የሐዘን ተካፋይነቱን ለመግለጥ መልእክተኞች ላከ። መልእክተኞቹም ሊያጽናኑት ወደ ዐሞን ምድር በደረሱ ጊዜ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዳዊ​ትም፥ “አባቱ ስላ​ደ​ረ​ገ​ልኝ ወረታ እኔ ለና​ዖስ ልጅ ለሐ​ናን ቸር​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ” አለ። ዳዊ​ትም አባቱ ስለ ሞተ ሊያ​ጽ​ና​ናው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ የዳ​ዊ​ትም አገ​ል​ጋ​ዮች ሊያ​ጽ​ና​ኑት ወደ ሐናን ወደ አሞን ልጆች ምድር መጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ዳዊትም “አባቱ ስላደረገልኝ ወረታ እኔ ለናዖስ ልጅ ለሐኖን ቸርነት አደርጋለሁ፤” አለ። ዳዊትም አባቱ ስለ ሞተ ሊያጽናናው መልእክተኞችን ላከ፤ የዳዊትም ባሪያዎች ሊያጽናኑት ወደ ሐኖን ወደ አሞን ልጆች ምድር መጡ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 19:2
14 Referencias Cruzadas  

ዳዊትም፥ “ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት የቀረ ሰው ይኖር ይሆን?” በማለት ጠየቀ።


ዳዊትም፥ “አትፍራ፤ ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ስል ቸርነት አደርግልሃለሁ። የአባትህን የሳኦልን ምድር በሙሉ እመልስልሃለሁ፤ ዘወትርም ከማዕዴ ትበላለህ” አለው።


ግያዝ “ለእኛ ስላደረገችው መልካም ነገር ሁሉ ምን አደርግላት ዘንድ እንደምትፈልግ ጠይቃት፤ ምናልባት ወደ ንጉሡ ወይም ወደ ጦር አዛዡ ዘንድ ሄጄ የምነግርላት ጉዳይ ሊኖር ይችላል” አለው። እርሷም “በዘመዶች መካከል በምኖርበት በዚህ ስፍራ ምንም የሚቸግረኝ ነገር የለም” ስትል መለሰችለት።


ከዚህም በኋላ የአሞናውያን ንጉሥ ናዖስ ሞተ፥ ልጁም በእርሱ ፋንታ ነገሠ።


የአሞን ልጆች ሹማምንት ግን ሐኖንን እንዲህ አሉት፦ “ዳዊት አባትህን አክብሮ የሚያጽናኑህን ወደ አንተ የላከ ይመስልሃልን? ባርያዎቹስ አገሪቱን ለመመርመር፥ ለማጥፋት፥ ለመሰለልም ወደ አንተ የመጡ አይደሉምን?”


በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ በሕዝቡ ጆሮ ከፍ ባለ ድምፅ አነበቡ፤ አሞናዊ ወይም ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ለዘለዓለም እንዳይገባ የሚል በዚያ ተጽፎ ተገኘ።


ወደ አምላካችን ጸለይን፥ በእነርሱም ምክንያት በሌሊትና በቀን በእነሱ ላይ ጠባቂ አቆምን።


እኔም ከቅጥሩ በስተ ኋላ በኩል ባለው በታችኛው ስፍራ ሰይፋቸውን፥ ጦራቸውንና ቀስታቸውን አስይዤ ሕዝቡን በየወገናቸው አቆምኳቸው።


ጠቢብ ድሀ ሰውም ተገኘባት፥ ያችንም ከተማ በጥበቡ አዳናት፥ ያን ድሀ ሰው ግን ማንም አላሰበውም።


ከአይሁድም ብዙዎች ስለ ወንድማቸው ሊያጽናኑአቸው ወደ ማርታና ወደ ማርያም መጥተው ነበር።


ዳዊት ወደ ጺቅላግ በመጣ ጊዜ፥ ወዳጆቹ ለሆኑት ለይሁዳ ሽማግሌዎች፥ “ከጌታ ጠላቶች የተማረከ ስጦታ እነሆ ይሄው፤” በማለት ከምርኮው ላይ ከፍሎ ላከላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos