አገልጋዮቹ ሁሉ፥ ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጌት አብረውት የመጡትን ስድስት መቶ ጌታውያን ሁሉን ጨምሮ ተሰልፈው በንጉሡ ፊት ዐለፉ።
1 ዜና መዋዕል 18:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፤ የዳዊትም ልጆች በንጉሡ አጠገብ አለቆች ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዮዳሄ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፈሊታውያን አዛዥ ነበር፤ የዳዊት ወንዶች ልጆቹ ደግሞ ከንጉሡ ቀጥሎ የበላይ ሹማምት ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮዳሄ ልጅ በናያ የዳዊት ክብር ዘብ አዛዥ ነበር፤ የንጉሥ ዳዊት ወንዶች ልጆች በአባታቸው መንግሥት ከፍተኛ ማዕርግ ነበራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ሹም ነበረ፤ የዳዊትም ልጆች በንጉሡ አጠገብ አለቆች ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮዳሄ ልጅ በናያስ በከሊታውያንና በፈሊታውያን ላይ ነበረ፤ የዳዊትም ልጆች በንጉሡ አጠገብ አለቆች ነበሩ። |
አገልጋዮቹ ሁሉ፥ ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጌት አብረውት የመጡትን ስድስት መቶ ጌታውያን ሁሉን ጨምሮ ተሰልፈው በንጉሡ ፊት ዐለፉ።
አቢሳንም ተከትለው የኢዮአብ ሰዎች ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን፥ እንዲሁም ሌሎች ኀያላን ጦረኞች በሙሉ ወጡ፤ የቢክሪ ልጅ ሼባዕን ለማሳደድ ከኢየሩሳሌም ወጡ።
ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን የዮዳሄም ልጅ በናያስ ከሊታውያንና ፈሊታውያንም ወረዱ፥ ሰሎሞንንም በንጉሡ በዳዊት በቅሎ ላይ አስቀምጠው ወደ ግዮን አመጡት።
ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ከሊታውያንንና ፈሊታውያንንም ላከ፥ በንጉሡም በቅሎ ላይ አስቀመጡት።
“ሥራቸውም የጌታን ቤት በየአደባባዩና በየጓዳው ውስጥ በሚሰጡተት አገልግሎት አሮንን ልጆች መርዳት፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት መሥራት ነበረ።
እናንተ በባሕር ዳር የምትኖሩ፥ የከሪታውያን ሕዝብ ወዮላችሁ! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፥ የጌታ ቃል በእናንተ ላይ ነው፥ የሚቀመጥብሽ እንዳይኖር አድርጌ አጠፋሻለሁ።