ከጌድሶን ልጆች፤ ከመቶ ሠላሳ ወንድሞቹ ጋር አለቃው ኢዮኤል ነበር፤
ከጌርሶን ዘሮች፣ አለቃውን ኢዩኤልንና አንድ መቶ ሠላሳ የሥጋ ዘመዶቹን፤
ከጌርሾን ጐሣ፥ ኢዮኤል መቶ ሠላሳ ለሚሆኑት የጐሣ አባሎች ተጠሪ ሆኖ መጣ፤
ከጌድሶን ልጆች፤ አለቃው ኢዮሔት፥ ወንድሞቹም መቶ ሠላሳ፤
ከጌድሶን ልጆች አለቃው ኢዮኤል፥ ወንድሞቹም መቶ ሠላሳ፤
ዳዊትም ካህናቱን ሳዶቅንና አብያታርን፥ ሌዋውያንንም ኡርኤልን፥ ዓሣያን፥ ኢዮኤልን፥ ሸማያን፥ ኤሊኤልን፥ አሚናዳብንም ጠራቸው፤
ከሜራሪ ልጆች፤ ከሁለት መቶ ሀያ ወንድሞቹ ጋር አለቃው ዓሣያ ነበር፤
ከኤሊጻፋን ልጆች፤ ከሁለት መቶ ወንድሞቹ ጋር አለቃው ሸማያ ነበር፤
የለአዳን ልጆች አለቃው ይሒኤል፥ ዜቶም፥ ኢዮኤል ሦስት ነበሩ።