በዚህ ጊዜ፥ “በእግዚአብሔር ታቦት ምክንያት የዖቤድ ኤዶም ቤተሰቡና ያለውን ሁሉ ጌታ ባረከለት” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ስለዚህ ዳዊት ወደዚያው ወርዶ፥ የእግዚአብሔርን ታቦት ከዖቤድኤዶም ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በታላቅ ደስታ አመጣው።
1 ዜና መዋዕል 15:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊትም ወዳዘጋጀለት ስፍራ የጌታን ታቦት ለማምጣት እስራኤልን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያመጡ እስራኤልን ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበሰበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዳዊት የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደተዘጋጀለት ስፍራ ለመውሰድ የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም አስጠራ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ወዳዘጋጀላት ስፍራ የእግዚአብሔርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስራኤልን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ወዳዘጋጀለት ስፍራ የእግዚአብሔርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስራኤልን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ። |
በዚህ ጊዜ፥ “በእግዚአብሔር ታቦት ምክንያት የዖቤድ ኤዶም ቤተሰቡና ያለውን ሁሉ ጌታ ባረከለት” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ስለዚህ ዳዊት ወደዚያው ወርዶ፥ የእግዚአብሔርን ታቦት ከዖቤድኤዶም ቤት ወደ ዳዊት ከተማ በታላቅ ደስታ አመጣው።
ከዚያም የጌታን ታቦት አምጥተው፥ ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ በተዘጋጀለት ስፍራ አኖሩት፤ ዳዊትም የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት በጌታ ፊት አቀረበ።
ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን የጌታን የቃል ኪዳን ታቦት ለማምጣት፥ ወደ ቤተ መቅደሱም ለማስገባት፥ የእስራኤል የነገድ መሪዎችና የጐሣ አለቆች ሁሉ እርሱ ወደሚገኝበት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ጠራ።
ዳዊትም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “መልካም መስሎ ቢታያችሁ፥ የጌታም የአምላካችን ፈቃድ ቢሆን፥ በእስራኤል አገር ሁሉ ለቀሩት ወንድሞቻችን በከተሞቻቸውና በመሰማሪያዎቻቸውም ለተቀመጡት ካህናትና ሌዋውያን ወደ እኛ እንዲሰበሰቡ እንላክባቸው፤
እነርሱንም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የሌዋውያን አባቶች ቤቶች አለቆች ናችሁ፤ ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ የእስራኤልን አምላክ የጌታን ታቦት እንድታመጡ እናንተና ወንድሞቻችሁ ተቀደሱ።
የእግዚአብሔርንም ታቦት ይዘው ገቡ፥ ዳዊትም በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕትም በጌታ ፊት አቀረቡ።
ሰሎሞንም ለእስራኤል ሁሉ፥ ለሻለቆች፥ ለመቶ አለቆችም፥ ለፈራጆችም፥ በእስራኤልም ሁሉ ዘንድ ለነበሩ መሳፍንት ሁሉ፥ ለአባቶች ቤቶች አለቆች ተናገረ።
በዚያን ጊዜም ሰሎሞን የጌታን ቃል ኪዳን ታቦት ከዳዊት ከተማ ከጽዮን እንዲያመጡ የእስራኤልን ሽማግሌዎችና የነገድ አለቆችን ሁሉ የእስራኤልንም ልጆች አባቶች ቤቶች መሳፍንት ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።