Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 15:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ስለዚህም ዳዊት የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደተዘጋጀለት ስፍራ ለመውሰድ የእስራኤልን ሕዝብ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም አስጠራ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያመጡ እስራኤልን ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበሰበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዳዊትም ወዳዘጋጀለት ስፍራ የጌታን ታቦት ለማምጣት እስራኤልን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዳዊ​ትም ወዳ​ዘ​ጋ​ጀ​ላት ስፍራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሰበ​ሰበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ዳዊትም ወዳዘጋጀለት ስፍራ የእግዚአብሔርን ታቦት ያመጣ ዘንድ እስራኤልን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 15:3
13 Referencias Cruzadas  

በቃል ኪዳኑ ታቦት ምክንያት እግዚአብሔር የዖቤድኤዶምን ቤተሰብና ያለውን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር የባረከለት መሆኑን ንጉሥ ዳዊት ሰማ፤ ስለዚህም የቃል ኪዳኑን ታቦት በታላቅ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ሊወስደው በማሰብ ወደ ዖቤድኤዶም ቤት ሄዶ አወጣው።


ታቦቱንም አምጥተው ዳዊት ባዘጋጀለት ድንኳን ውስጥ በተመደበለት ስፍራ አኖሩት፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ።


ከዚህ በኋላ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን ለማምጣትና ወደ ቤተ መቅደሱ ለማስገባት የእስራኤል የነገድ መሪዎችና የጐሣ አለቆች ሁሉ እርሱ ወደሚገኝበት ወደ ኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ጠራ፤


ከዚያም በኋላ ለመላው የእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ሲል አስታወቀ፥ “እናንተ ከተስማማችሁበትና የአምላካችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ፥ የቀሩት የአገራችን ሰዎች፥ ካህናትና ሌዋውያን ወደሚኖሩባቸው ታናናሽ ከተማዎች መልእክተኞች ልከን ወደዚህ መጥተው ከእኛ ጋር እንዲሰበሰቡ እንንገራቸው፤


ስለዚህም ዳዊት የቃል ኪዳኑን ታቦት ከቂርያትይዓሪም ወደ ኢየሩሳሌም ለማምጣት በደቡብ በኩል እስከ ግብጽ ግዛት ድንበር፥ በሰሜን እስከ ሐማት መተላለፊያ ድረስ በመላው እስራኤል የሚገኘውን ሕዝብ በአንድነት ሰበሰበ።


ዳዊት የሚኖርባቸውን ቤቶች በራሱ ከተማ በኢየሩሳሌም ሠራ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት የሚኖርበትንም ስፍራ አዘጋጅቶ ድንኳን ተከለለት፤


ሌዋውያኑንም እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ እናንተ ለሌዋውያን ጐሣዎች መሪዎች ናችሁ፤ የእስራኤል አምላክን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት እኔ ወዳዘጋጀሁለት ስፍራ ተሸክማችሁ ታመጡ ዘንድ ራሳችሁንና ሌዋውያን ወገኖቻችሁን ሁሉ ቀድሱ፤


የቃል ኪዳኑንም ታቦት ወስደው ዳዊት ባዘጋጀው ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ ከዚያም በኋላ በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንና የኅብረት መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር አቀረቡ፤


ንጉሥ ሰሎሞን ለእስራኤላውያን ሁሉ፥ ለሺህ አለቆችና ለመቶ አለቆች፥ እንዲሁም ለመንግሥቱ ባለ ሥልጣኖች፥ ለቤተሰብ መሪዎችና ሕዝብ በሙሉ፥


የቃል ኪዳኑ ታቦት ግን ንጉሥ ዳዊት ከቂርያትይዓሪም ባመጣው ጊዜ በኢየሩሳሌም አዘጋጅቶለት በነበረው ድንኳን ውስጥ ይገኝ ነበር።


ከዚህ በኋላ ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት የዳዊት ከተማ ከሆነችው ከጽዮን ወደ ቤተ መቅደሱ ያመጡ ዘንድ የእስራኤል ሽማግሌዎች፥ የነገድና የቤተሰብ አለቆች ሁሉ በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ ትእዛዝ ሰጠ።


ሁለቱንም የድንጋይ ጽላቶች ወስዶ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ አስቀመጣቸው፤ መሎጊያዎችንም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ አስገባ፤ የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ አኖረ፤


እነርሱም ሙሴ ያዘዛቸውን ሁሉ ወደ ድንኳኑ ፊት ለፊት አመጡ፤ ማኅበሩም ሁሉ ለእግዚአብሔር ለመስገድ ወደዚያ ተጠግተው ቆሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos