1 ዜና መዋዕል 12:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጺቅላግም ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት የመጡ እነዚህ ናቸው፤ በጦርነትም ካገዙት ኃያላን መካከል ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ከቂስ ልጅ ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በጺቅላግ ሳለ ወደ እርሱ የመጡት ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ እነርሱም በጦርነቱ ላይ ከረዱት ተዋጊዎች መካከል ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት ከቂስ ልጅ ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በጺቅላግ በነበረ ጊዜ ከእርሱ ጋር የተቀላቀሉት ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ ከእነርሱም መካከል የጦር ጀግኖች ነበሩባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሴቅላቅም ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት የመጡ እነዚህ ናቸው፤ በጦርነትም ባገዙት ኀያላን መካከል ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጺቅላግም ከቂስ ልጅ ከሳኦል በተሸሸገ ጊዜ ወደ ዳዊት የመጡ እነዚህ ናቸው፤ በሰልፍም ባገዙት ኀያላን መካከል ነበሩ። |
የምሥራች ያመጣልኝ መስሎት፥ ‘ሳኦል ሞተ’ ብሎ የነገረኝን ሰው ይዤ ጺቅላግ ላይ ገደልሁት፤ ለዚያ ሰው ስላመጣው ምሥራች የሸለምሁት ይህን ነበር።
ለዳዊትም የነበሩት የኃያላን አለቆች እነዚህ ናቸው፤ ስለ እስራኤል እንደ ተናገረው እንደ ጌታ ቃል ሊያነግሡት ከእስራኤል ሁሉ ጋር በመንግሥቱ ላይ አጸኑት።
እርሱም እንዲህ አለ፦ “ይህን እንዳደርግ አምላኬ አይፈቅድልኝም፤ በነፍሳቸው የደፈሩትን የእነዚህን ሰዎች ደም እጠጣለሁን? ነፍሳቸውን አደጋ ላይ ጥለው አምጥተውታል።” ስለዚህም ሊጠጣው አልፈለገም። ሦስቱም ኃያላን ያደረጉት ይህ ነው።