ኢያሱ 16:4 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍም ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን ወረሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ የዮሴፍ ዘሮች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን ተቀበሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሴፍም ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን ወረሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን እንደሚከተለው ተቀበሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሴፍም ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ርስታቸውን ወረሱ። |
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ርስት አድርጋችሁ ለአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ምድሪቱን የምትከፍሉበት ድንበር ይህ ነው። ለዮሴፍ ሁለት እድል ፈንታ ይሆናል።
የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፥ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንሰሶቻቸውና ለከብቶቻቸውም ከሚሆን መሰምርያቸው በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም።
የኤፍሬምም ልጆች ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፥ በምሥራቅ በኩል የርስታቸው ድንበር አጣሮትአዳር እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ድረስ ነበረ፥
የዮሴፍ ልጆች ኢያሱን፦ እኔ ብዙ ሕዝብ ስለ ሆንሁ እስከ አሁንም እግዚአብሔር ስለ ባረከኝ ለምን አንድ ክፍል አንድም ዕጣ ብቻ ርስት አድርገህ ሰጠኸኝ? አሉት።