ወደ ግብፅ ሀገር በሄደ ጊዜ ለዮሴፍ ምስክርን አቆመ። የማያውቀውን ቋንቋ ሰማ።
የእንባ እንጀራ አበላሃቸው፤ ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው።
የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ በሕዝብህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈጣለህ?
ሐዘንን እንደ ምግብ፥ እንባንም እንደ መጠጥ በብዛት ሰጠሃቸው።
ሰውነቴ ማረፍ አልቻለችም፤ የሥጋዬን ክርፋት እንደ አንበሳ ክርፋት እመለከተዋለሁና።
ሁልጊዜም አይቀሥፍም፥ ለዘለዓለምም አይቈጣም።
ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፤ እነርሱም ይምሩኝ፥ አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።
አቤቱ አመሰግንሃለሁ፤ አመሰግንሃለሁ ስምህንም እጠራለሁ፤ ተአምራትህን ሁሉ እናገራለሁ።
የእንባችንን እንጀራ ትመግበናለህ፥ እንባችንንም በስፍር ታጠጣናለህ።
እግዚአብሔርም የጭንቀትን እንጀራና የመከራን ውኃ ይሰጥሃል። የሚያሳስቱህም እንግዲህ ወደ አንተ አይቀርቡም፤ ዐይኖችህ ግን የሚያሳስቱህን ያያሉ፤
ሳምኬት። በቍጣህ ከደንኸን፤ አሳደድኸንም፤ ገደልኸን፤ አልራራህልንም።
ጸሎታችን እንዳያርግ ራስህን በደመና ከደንህ።