ነገር ግን እርሱን መበደልን እንደገና ደገሙ፥ ልዑልንም በምድረ በዳ አስመረሩት።
ደመናት ውሃን አንጠባጠቡ፤ ሰማያት አንጐደጐዱ፤ ፍላጾችህም ዙሪያውን አብለጨለጩ።
አቤቱ፥ ውኆች አዩህ፥ ውኆችም አይተውህ ፈሩ፥ ጥልቆችም ተነዋወጡ።
ደመናዎች ዝናብን አዘነቡ፤ ነጐድጓድ በሰማይ አስገመገመ፤ የመብረቅ ፍላጻዎችህም ከላይ ከሰማይ አንጸባረቁ።
ፍላጻውን ላከ፤ በተናቸውም፤ መብረቅንም አሰምቶ አስደነገጣቸው።
የሞት ጣር ያዘኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፤ ጭንቀትና መከራ አገኘኝ።
“ኀይልህ ግሩም ነው” ይላሉ፥ ግርማህንም ይነጋገራሉ፥ ብርታትህንም ያስረዳሉ።
የአንደበቴ ቃል ያማረ ይሁን፤ የልቤ ዐሳብም ሁልጊዜ በፊቴ ነው አቤቱ ረድኤቴ መድኀኒቴም።
እግዚአብሔር ድሆችን ሰምቶእቸዋልና፥ እስረኞችንም አልናቃቸውምና።
ተራሮች አንተን አይተው ተጨነቁ፣ የውኃ ሞገድ አልፎአል፣ ቀላዩም ድምፁን ሰጥቶአል፥ እጁንም ወደ ላይ አንሥቶአል።
ፍላጾችህ ከወጡበት ብርሃን የተነሣ፥ ከሚንቦገቦገውም ከጦርህ ፀዳል የተነሣ፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቆሙ።
አቤቱ! ከሴይር በወጣህ ጊዜ፥ ከኤዶምያስም ሜዳ በተራመድህ ጊዜ፥ ምድሪቱ ተናወጠች፤ ሰማያትም ጠልን አንጠባጠቡ፤ ደመናትም ደግሞ ውኃን አንጠባጠቡ።