አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።
ቀኑን ሙሉ ተቀሠፍሁ፤ ጧት ጧትም ተቀጣሁ።
ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው።
ቀኑን ሙሉ ተሠቃየሁ፤ በየማለዳውም ተቀጣሁ።
ዳግመኛም ከጥንት ጀምሮ ትመረምረኛለህ፤ ታላቅ መቅሠፍትን አመጣህብኝ። ፈተናዎችንም ላክህብኝ።
ኀጢኣተኛ ብሆን በአንተ ዘንድ መልካም ነውን? የእጅህን ሥራ ቸል ብለሃልና፤ የኃጥኣንንም ምክር ተመልክተሃልና።
ማለዳ ማለዳስ ትጐበኘው ዘንድ፥ በዕረፍቱም ትፈርድለት ዘንድ፥
በግፍ የሚጠሉኝ በላዬ ደስ አይበላቸው፥ በከንቱ የሚጠሉኝና በዐይናቸው የሚጠቃቀሱብኝም።
የሚያሳዝኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበረታሉ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ አልሽርም አለ? እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃም ሆነብኝ።
“እኔ ከምድር አሕዛብ ሁሉ እናንተን ብቻችሁን አውቄአችኋለሁ፤ ስለዚህ ስለ ኀጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።”
እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር፥ “ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም።
በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፤ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።