መዝሙር 62:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነፍሴ በኋላህ ተከታተለች፥ እኔንም ቀኝህ ተቀበለችኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎች ሆይ፤ ሁልጊዜ በርሱ ታመኑ፤ ልባችሁን በፊቱ አፍስሱ፤ እግዚአብሔር መጠጊያችን ነውና። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፥ ጠንካራ ዓለቴና መጠለያዬ እግዚአብሔር ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቦች ሆይ! ዘወትር በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ መጠጊያችን ስለ ሆነ የልባችሁን ሐሳብ ሁሉ ለእርሱ አቅርቡ። |
ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ፥ ጐልማስነቴንም ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬ እገባለሁ፤ አቤቱ፥ አምላኬ፥ በመሰንቆ አመሰግንሃለሁ።
ከእናንተ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ማን ነው? የባሪያውንም ቃል ይስማ፤ በጨለማም የምትሄዱ፥ ብርሃንም የሌላችሁ በእግዚአብሔር ስም ታመኑ፤ በእግዚአብሔርም ተደገፉ፤
ቆፍ። ተነሺ፤ በሌሊት በመጀመሪያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፤ በጎዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።
የእግዚአብሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይቻልም፤ በእርሱ ለተማፀን ተጠብቆልን ባለ ተስፋችንም ማመንን ላጸናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።
ሐናም መልሳ እንዲህ አለችው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ አይደለም፤ እኔስ ወራት የባሳት ሴት ነኝ፤ ጠጅና ሌላ የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈሰስሁ፤