ሰውነቴ ወደ ምድር ተጣበቀች፤ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አድነን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አሳካልን።
አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፥ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና።
እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አድነን! እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ ሁሉ ነገር የተሟላ እንዲሆን አድርግልን!
ፊትህ በተቈጣ ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድርጋቸው፤ አቤቱ፥ በቍጣህ አውካቸው፥ እሳትም ትብላቸው።
አቤቱ፥ እኔን ለማዳን ተመልከት፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።