አለቆች ደግሞ ተቀምጠው እኔን አሙኝ፤ ባሪያህ ግን ፍርድህን ያሰላስል ነበር።
እግዚአብሔር ይህን አድርጓል፤ ይህም ለዐይናችን ድንቅ ነው።
ይህች ከጌታ ዘንድ ሆነች፥ ለዓይናችንም ድንቅ ናት።
ይህም የእግዚአብሔር ሥራ ነው፤ ለዐይኖቻችንም ድንቅ ነው።
እርሱ የማይመረመረውን ታላቅ ነገርና የማይቈጠረውን የከበረና ድንቅ ነገር ያደርጋል።
ይህም ደግሞ ድንቅ ምክርን ከሚመክር በግብሩም ገናና ከሆነው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ወጥቶአል። እናንተ ግን ከንቱ መጽናናትን ታበዙ ዘንድ ትሻላችሁ።
‘እነሆ፥ እናንተ የምታቃልሉ፥ እዩ፤ ተደነቁም፤ ያለዚያ ግን ትጠፋላችሁ፤ ማንም ቢነግራችሁ የማታምኑትን ሥራ እኔ በዘመናችሁ እሠራለሁና።’ ”
ጴጥሮስና ዮሐንስም ግልጥ አድርገው ሲናገሩ ባዩአቸው ጊዜ፥ ያልተማሩና መጽሐፍን የማያውቁ ሰዎች እንደ ሆኑ ዐውቀው አደነቁ፤ ሁልጊዜም ከኢየሱስ ጋር እንደ ነበሩ ዐወቁ።