መዝሙር 105:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ጊዜ አዳናቸው፤ እነርሱ ግን በምክራቸው አስመረሩት፥ በኀጢአታቸውም መከራ ተቀበሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡን በደስታ፣ ምርጦቹንም በእልልታ አወጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቡንም በደስታ የተመረጡትንም በእልልታ አወጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የተመረጠውን ሕዝቡን መርቶ አወጣ፤ እነርሱም በደስታ ዘመሩ፤ እልልም አሉ። |
እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንንና የሹሞቹን ልብ አጸና፤ እርሱም የእስራኤልን ልጆች አሳደደ፤ የእስራኤልም ልጆች ከፍ ባለች እጅ ወጡ።
በእግዚአብሔር የተሰበሰቡም ይመለሳሉ፤ በደስታም ተመልሰው ወደ ጽዮን ይመጣሉ፤ የዘለዓለም ደስታም በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ሐሤትንና ደስታንም ያገኛሉ፤ መከራ፥ ኀዘንና ትካዜም ይጠፋሉ።
እናንተም በደስታ ትወጣላችሁ፤ በሐሤትም ትማራላችሁ፤ ተራሮችና ኮረብቶች በደስታ ሊቀበሏችሁ ይዘላሉ፤ የሜዳም ዛፎች ሁሉ በቅርንጫፎቻቸው ያጨበጭባሉ።
የእስራኤል ሕዝብ አምላክ አባቶቻችንን መረጣቸው፤ ወገኖቹንም በተሰደዱበት በምድረ ግብፅ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ ከዚያም ከፍ ባለ ክንዱ አወጣቸው።
ከግብፃውያንም እጅ ከሚጋፉአችሁም ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ፤ ከፊታችሁም አሳደድኋቸው፤ ሀገራቸውንም ሰጠኋችሁ፤