ለሚያገኙአቸው ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ናቸውና።
ለሚያገኘው ሕይወት፤ ለመላው የሰው አካልም ጤንነት ነውና።
ለሚያገኙአቸው ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና።
እነርሱም ለሚያስተውሉአቸው ሕይወትን፥ ለመላ ሰውነትም ጤንነትን ይሰጣሉ።
በሐሰት የሚመሰክሩ በሰይፍ ይገድላሉ፤ በአፋቸው ሰይፍ አለና። የጠቢባን ምላስ ግን የቈሰለውን ይፈውሳል።
ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ጣፋጭነቱም የነፍስ መድኀኒት ነው።
ነፍስህ ትድን ዘንድ፥ ለአንገትህም ሞገስ ይሆንህ ዘንድ። ለሥጋህ ፈውስ፥ ለአጥንትህም ጠገን ይሆንልሃል።
ይህም ለሥጋህ ፈውስ፥ ለአጥንትህም ጠገን ይሆንልሃል።
ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ንግግሬንም ተቀበል፤ የሕይወትህም ዓመታት ይበዙልሃል፥ የሕይወትህ መንገድ ይበዛ ዘንድ።
ያስተምሩኝም ነበር፥ እንዲህም ይሉኝ ነበር፦ ቃላችን በልብህ ይኑር፤ ትእዛዞቻችንንም ጠብቅ፥ አትርሳቸውም።
መንገዶቼ የሕይወት መንገዶች ናቸውና። እኔን ያገኘ ሕይወትን አገኘ፤ ፈቃዱም በእግዚአብሔር ዘንድ ይዘጋጃል።
እነሆ ፈውስንና መድኀኒትን እሰጣታለሁ፤ እፈውሳታለሁም፤ የሰላምንና የእውነትንም መንገድ እገልጥላቸዋለሁ።