ምሳሌ 19:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለድሃ ቸርነትን የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል፥ እንደ ስጦታውም መልሶ ይከፍለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለድኻ የሚራራ ለእግዚአብሔር ያበድራል፤ ስላደረገውም ተግባር ዋጋ ይከፍለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለጌታ ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለድኾች የሚሰጥ ለእግዚአብሔር እንዳበደረ ይቈጠራል፤ እግዚአብሔርም የመልካም ሥራውን ዋጋ ይከፍለዋል። |
ለድሃ የሚራራ እርሱ ይበላል እንጀራውን ለድሃ ሰጥቶአልና። ለሰጠው ሀብታምም የሚከፍል አይደለምና። መማለጃን የሰጠ ሰው ድል መንሣትንና ሞገስን ያገኛል፥ ነገር ግን የተቀበለውን ነፍስ ያጠፋል።
ስጡ፥ ይሰጣችኋልም፤ የሞላና የበዛ፥ የተትረፈረፈም መልካም መስፈሪያ በዕቅፋችሁ ይሰጡአችኋል፤ በሰፈራችሁበትም መስፈሪያ ይሰፍሩላችኋል።”
“የእርሻህን መከር ባጨድህ ጊዜ ነዶም ረስተህ በእርሻህ ብታስቀር፥ ትወስደው ዘንድ አትመለስ፤ አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ፥ ለመጻተኛና ለድሃ-አደግ፥ ለመበለትም ተወው።
እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስለ አገለገላችሁ፥ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው ያደረጋችትሁን ሥራ፥ በስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።