Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 19:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ትእዛዛትን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፤ መንገዶቹን የሚያቃልል ግን ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ትእዛዞችን የሚያከብር ሕይወቱን ይጠብቃል፤ መንገዱን የሚንቅ ግን ይሞታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ትእዛዝን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል፥ መንገዱን ቸል የሚል ግን ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ትእዛዝን የሚጠብቅ በሕይወት ይኖራል፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሚንቅ ግን ይጠፋል።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 19:16
25 Referencias Cruzadas  

ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “መል​ካም መል​ሰ​ሃል፤ እን​ዲሁ አድ​ርግ፤ ትድ​ና​ለ​ህም” አለው።


የእግዚአብሔርን ሥራ የሚያቃልለውን እርሱ ያቃልለዋል፥ ትእዛዙን የሚሰማ ግን በእርሱ በሕይወት ይኖራል። ለውሸተኛ ልጅ ምንም ደግነት የለም፥ ለብልህ አገልጋይ ግን ሥራው መልካም ይሆናል። መንገዱም ይቃናል።


እር​ሱም፥ “ብፁ​ዓ​ንስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰም​ተው የሚ​ጠ​ብቁ ናቸው” አላት።


ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።


ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።


አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።


የሕይወት መንገዶች ከክፉ ያርቃሉ፤ የጽድቅ ጎዳና የዘመን ብዛት ነው። ትምህርትን የሚቀበል በበጎ ይኖራል። ተግሣጽን የሚጠብቅም ብልሃተኛ ይሆናል። መንገዶቹን የሚጠብቅ ሰውነቱን ይጠብቃል፥ ሕይወትንም የሚወድድ አፉን ይጠብቃል።


ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ መጠ​በቅ ነው እንጂ መገ​ዘ​ርም አይ​ጠ​ቅ​ምም፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም አይ​ጎ​ዳም።


የነ​ገ​ሩን ሁሉ ፍጻሜ ስማ፤ ይህ የሰው ሁለ​ን​ተ​ናው ነውና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍራ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ጠብቅ።


ትእ​ዛ​ዝን የሚ​ጠ​ብቅ ክፉን ነገር አያ​ው​ቅም፤ የጠ​ቢ​ብም ልብ የፍ​ር​ድን ጊዜ ያው​ቃል።


ልጄ ሆይ! ሕጎቼን አትርሳ፥ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ።


“ከወ​ደ​ዳ​ች​ሁ​ኝስ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ።


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ ሰምቶ ስላ​ል​ተ​ጠ​ነ​ቀቀ ደሙ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ ቢጠ​ነ​ቀ​ቅስ ኖሮ ነፍ​ሱን በአ​ዳነ ነበር።


ነገር ግን፦ ቃሌን ስሙ፤ እኔ አም​ላክ እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም ሕዝብ ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ፤ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ላ​ችሁ ዘንድ ባዘ​ዝ​ኋ​ችሁ መን​ገድ ሂዱ ብዬ በዚህ ነገር አዘ​ዝ​ኋ​ቸው።


እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ያመልጣል።


ከተግሣጽ የሚከላከል ራሱን ይጠላል። ተግሣጽን የሚወድድ ግን ራሱን ይወድዳል።


ረጃ​ጅም ተራ​ራ​ዎች ለዋ​ሊ​ያ​ዎች፥ ድን​ጋ​ዮ​ችም ለአ​ሽ​ኮ​ኮ​ዎች መሸሻ ናቸው።


ሰነ​ፉን ሰው ቍጣ ይገ​ድ​ለ​ዋ​ልና፥ ቅን​ዓ​ትም ሰነ​ፉን ያጠ​ፋ​ዋል።


ከጽድቅ መንገድ የሚሳሳት ሰው፥ በረዐይት ጉባኤ ያርፋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios