አላዋቂ ጥበብን ቢጠይቅ ጥበብ ይሆነዋል፤ ዝም የሚል ሰውም ጥበበኛን ይመስላል።
ቂል እንኳ ዝም ቢል ጠቢብ፣ አንደበቱንም ቢገዛ አስተዋይ ይመስላል።
ሰነፍ ዝም ቢል ጠቢብ ሆኖ ይቈጠራል፥ ከንፈሩንም የሚቈልፍ፦ ባለ አእምሮ ነው ይባላል።
ሞኝ ዝም ሲል ጥበበኛ ይመስላል፤ ምንም ሳይናገር ቢቀር እንደ ብልኅ ይቈጠራል።
ላዳምጣችሁ አይገባኝም፥ ጥበብ ከእናንተ ጠፍታለችና።
እኔ በትዕግሥት ጠበቅሁ እንጂ አልተናገርሁም። እናንተ ዝም ብላችሁ ቆማችሁ፥ አልመለሳችሁምና።”
የጠቢባን ምላስ መልካም ነገርን ታውቃለች፤ የአላዋቂዎች አፍ ግን ክፋትን ይናገራል።
ከወዳጆቹ መለየትን የሚወድድ ሰው ምክንያትን ይፈልጋል፥ ሁልጊዜም ለሽሙጥ ይሆናል።
ሰነፍ ነገርን ያበዛል፤ ሰውም የሆነውንና ወደ ፊት የሚሆነውን አያውቅም፤ ከእርሱ በኋላ የሚሆነውንስ ማን ይነግረዋል?
ደግሞም ሰነፍ በልቡ ፈቃድና መንገድ በሚሄድ ጊዜ አእምሮ ይጐድለዋል፥ የሚያስበውም ሁሉ ሰንፍና ነው።
ሕልም በብዙ መከራ፥ እንዲሁም የሰነፍ ቃል በብዙ ነገር ይመጣልና።