La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ምሳሌ 17:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁልጊዜ ወዳጅ ይኑርህ፥ ወንድሞች በመከራ ጊዜ ጠቃሚዎች ይሆናሉ፥ ስለዚህ ይወለዳሉና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ወዳጅ ምን ጊዜም ወዳጅ ነው፤ ወንድምም ለክፉ ቀን ይወለዳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወዳጅ በዘመኑ ሁሉ ይወድዳል፥ ወንድምም ለመከራ ይወለዳል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወዳጅ ምን ጊዜም ቢሆን ወዳጁን ይወዳል፤ ወንድም የሚወለደው የወንድሙን ችግር ለመካፈል ነው።

Ver Capítulo



ምሳሌ 17:17
16 Referencias Cruzadas  

ወን​ድሜ ዮና​ታን ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ አንተ በእኔ ዘንድ እጅግ የተ​ወ​ደ​ድህ ነበ​ርህ፤ ከሴት ፍቅር ይልቅ ፍቅ​ርህ ለእኔ ድንቅ ነበረ።


ኤቲም ለን​ጉሡ መልሶ፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! በጌ​ታ​ዬም በን​ጉሡ ሕይ​ወት እም​ላ​ለሁ! ጌታዬ ባለ​በት ስፍራ ሁሉ፥ በሞ​ትም ቢሆን በሕ​ይ​ወ​ትም፥ በዚያ ደግሞ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ እሆ​ና​ለሁ” አለው።


ጠማማ ሰው ክፋትን ይዘራል፥ የሐሰት መብራት ክፉዎችን ታቃጥላቸዋለች፥ ወዳጆችንም ትለያለች።


አላዋቂ ልጅ ለአባቱ ኀፍረት ነው፥ ከዐስበ ደነስ ጋር የሚቀርብ ስእለትም ንጹሕ አይደለም።


ድሃ ወንድሙንም የሚጠላ ሰው ሁሉ፥ ከወንድምነቱ የራቀ ነው። በጎ ዕውቀትም ወደሚያውቋት ትቀርባለች። ብልህ ሰውም ያገኛታል። ብዙ ክፋትን የሚሠራ ክፋትን ይፈጽማል፥ ስቅጥጥ የሚያደርግ ነገርን የሚናገርም አይድንም።


እነ​ር​ሱን የቀ​ደ​ሳ​ቸው እርሱ፥ የተ​ቀ​ደ​ሱት እነ​ር​ሱም ሁሉም በአ​ን​ድ​ነት ከአ​ንዱ ናቸ​ውና። ስለ​ዚ​ህም እነ​ር​ሱን፥ “ወን​ድ​ሞች” ማለ​ትን አያ​ፍ​ርም።


ሩትም፦ ወደምትሄጅበት እሄዳለሁና፥ በምታድሪበትም አድራለሁና እንድተውሽ ከአንቺም ዘንድ እንድመለስ አታስቸግሪኝ፣ ሕዝብሽ ሕዝቤ፥ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል፣


ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ስለ ወደ​ደው ዮና​ታ​ንና ዳዊት ቃል ኪዳን አደ​ረጉ።


ዮና​ታ​ንም፥ “አባቴ ሳኦል ሊገ​ድ​ልህ ፈል​ጎ​አል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ለነ​ገው ተጠ​ን​ቅ​ቀህ ተሸ​ሸግ፤ በስ​ው​ርም ተቀ​መጥ።


እኔም እወ​ጣ​ለሁ፤ አን​ተም ባለ​ህ​በት እርሻ በአ​ባቴ አጠ​ገብ እቆ​ማ​ለሁ፤ ስለ አን​ተም ለአ​ባቴ እነ​ግ​ረ​ዋ​ለሁ፤ የሆ​ነ​ው​ንም አይቼ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ” ብሎ ለዳ​ዊት ነገ​ረው።


ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን እንደ ነፍሱ ይወ​ድድ ነበ​ርና እንደ ገና ማለ​ለት።


የሳ​ኦ​ልም ልጅ ዮና​ታን ተነ​ሥቶ ወደ ዳዊት ወደ ቄኒ ሄደ። እጁ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አጸና።