በሌሊትም ተነሣሁ፤ ከእኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርም ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ በልቤ ያኖረውን ለማንም አላስታወቅሁም፤ ተቀምጬበት ከነበረው እንስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እንስሳ አልነበረም።
ምሳሌ 12:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብልህ ሰው የጥበብ መንበር ነው፤ የሰነፎች ልብ ግን መርገምን ያገኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስተዋይ ሰው ዕውቀቱን ይሰውራል፤ የሞኞች ልብ ግን ቂልነትን ይነዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብልህ ሰው እውቀትን ይሸሽጋል፥ የሰነፎች ልብ ግን ስንፍናን ያወራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስተዋይ ሰዎች “ዐዋቂዎች ነን” እያሉ አይመጻደቁም፤ ሞኞች ግን “ዐዋቂዎች ነን” በማለት ድንቊርናቸውን ይገልጣሉ። |
በሌሊትም ተነሣሁ፤ ከእኔም ጋር ጥቂት ሰዎች ነበሩ፤ እግዚአብሔርም ለኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ በልቤ ያኖረውን ለማንም አላስታወቅሁም፤ ተቀምጬበት ከነበረው እንስሳ በቀር ከእኔ ጋር ምንም እንስሳ አልነበረም።
ጠባቆች ግን ወዴት እንደ ሄድሁ፥ ምን እንዳደረግሁም አላወቁም ነበር፤ ለአይሁድና ለካህናቱ፥ ለታላላቆችና ለሹሞቹም፥ ሥራም ይሠሩ ለነበሩት ለሌሎች እስከዚያ ጊዜ ገና አልተናገርሁም ነበር።