La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 7:89 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን እር​ሱን ለመ​ነ​ጋ​ገር በገባ ጊዜ በቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ ካለው ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛው በላይ ከኪ​ሩ​ቤ​ልም መካ​ከል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ይና​ገር ነበር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋራ ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ ከምስክሩ ታቦት መክደኛ በላይ በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ድምፅ ሲናገረው ሰማ፤ አነጋገረውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴም ከጌታ ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ በምስክሩ ታቦት ላይ ካለው ከስርየት መክደኛ በላይ ከኪሩቤልም መካከል ድምፁ ሲናገረው ይሰማ ነበር፤ እንዲህም እርሱ ተናገረው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በኪሩቤል መካከል ካለው ከቃል ኪዳኑ ታቦት መክደኛ በላይ ሆኖ ሲናገረው ሰማ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሙሴም ወደ መገናኛው ድንኳን እርሱን ለመነጋገር በገባ ጊዜ በምስክሩ ታቦት ላይ ካለው ከስርየት መክደኛ በላይ ከኪሩቤልም መካከል ድምፁ ሲናገረው ይሰማ ነበር፤ እርሱም ይናገረው ነበር።

Ver Capítulo



ዘኍል 7:89
15 Referencias Cruzadas  

በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ውስጥ ቁመ​ታ​ቸው ዐሥር ክንድ የሆነ ከወ​ይራ እን​ጨት ሁለት ኪሩ​ቤ​ልን ሠራ።


በረ​ዳ​ታ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ ይበ​ላ​ችሁ፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እልል በሉ።


በም​ድር ሁሉ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እልል በሉ፥


ደመ​ና​ውም የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ከደነ፤ ድን​ኳ​ን​ዋም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ተሞ​ላች።


ደመ​ና​ውም በላዩ ስለ​ነ​በር ድን​ኳ​ኑም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ስለ ተሞላ ሙሴ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ይገባ ዘንድ አል​ቻ​ለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ፥ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን፥ ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እኔም እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ያም አነ​ጋ​ግ​ር​ሃ​ለሁ፤ በአ​ንተ ካለ​ውም መን​ፈስ ወስጄ በእ​ነ​ርሱ ላይ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ አን​ተም ብቻ እን​ዳ​ት​ሸ​ከም የሕ​ዝ​ቡን ሸክም ከአ​ንተ ጋር ይሸ​ከ​ማሉ።


እኔ አፍ ለአፍ በግ​ልጥ እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በስ​ው​ርም አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ክብር ያያል፤ አገ​ል​ጋዬ ሙሴን ማማ​ትን ስለ ምን አል​ፈ​ራ​ች​ሁም?” አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


እን​ግ​ዲህ ምሕ​ረ​ትን እን​ድ​ን​ቀ​በል፥ በሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ንም ጊዜ የሚ​ረ​ዳ​ንን ጸጋ እን​ድ​ና​ገኝ፥ ወደ ጸጋው ዙፋን በእ​ም​ነት እን​ቅ​ረብ።


ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።


ሕዝ​ቡም ወደ ሴሎ ላኩ፤ በኪ​ሩ​ቤ​ልም ላይ የሚ​ቀ​መ​ጠ​ውን የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ከዚያ አመጡ፤ ሁለ​ቱም የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።