ከበጎችም የእግዚአብሔር ግብር ስድስት መቶ ሰባ አምስት ነበረ።
ከእነዚህም በጎችና ፍየሎች ለእግዚአብሔር የተሰጠ ግብር ስድስት መቶ ሰባ ዐምስት ነበር።
ከበጎችም የጌታ ግብር ስድስት መቶ ሰባ አምስት ነበረ።
ከእነዚህም ስድስት መቶ ሰባ አምስቱ ለእግዚአብሔር መባ ሆነው የተሰጡ ነበሩ፤
ከበጎችም የእግዚአብሔር ግብር ስድስት መቶ ሰባ አምስት ነበረ።
በዘመቻም ለነበሩ ሰዎች ድርሻ የሆነ እኩሌታ ከበግ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ሺህ አምስት መቶ በጎች ነበሩ፤
በሬዎችም ሠላሳ ስድስት ሺህ ነበሩ፤ የእግዚአብሔርም ግብር ሰባ ሁለት ነበረ።
አምላክህ እግዚአብሔር የባረከህን ያህል እጅህ መስጠት በምትችለው መጠን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሰባቱን ሱባዔ በዓል ታደርጋለህ።