ከሚካኑበትም አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ወግ የሚሆን ለመሥዋዕት የተለየውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ።
ዘኍል 31:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከድርሻቸው እኩሌታ ወስደህ የእግዚአብሔርን ቀዳምያት ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጠዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህንም ግብር ከድርሻቸው ላይ ወስደህ የእግዚአብሔር ፈንታ በማድረግ ለካህኑ ለአልዓዛር ስጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከድርሻቸው ወስደህ ለጌታ እንደ ስጦታ ቁርባን አግርህ ለካህኑ ለአልዓዛር ትሰጠዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእኔ ለእግዚአብሔር ልዩ ስጦታ በማድረግም ለካህኑ ለአልዓዛር ስጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከድርሻቸው ወስደህ ለእግዚአብሔር ለማንሣት ቍርባን ለካህኑ ለአልዓዛር ስጠው። |
ከሚካኑበትም አውራ በግ የተወሰደ ለአሮንና ለልጆቹ ወግ የሚሆን ለመሥዋዕት የተለየውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ።
“ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ከእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን ዐሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥ እናንተምከእርሱ ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ የዐሥራት ዐሥራት ታቀርባላችሁ።
እንዲሁ እናንተ ደግሞ ከእስራኤል ልጆች ከምትቀበሉት ዐሥራት ሁሉ ለእግዚአብሔር መባ አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ የእግዚአብሔርንም መባ ለይታችሁ ለካህኑ ለአሮን ትሰጣላችሁ።
ከእነዚያም ከተዋጉት፥ ወደ ሰልፍም ከወጡት ሰልፈኞች ዘንድ ከሰዎችም፥ ከበሬዎችም፥ ከበጎችም፥ ከአህዮችም፥ ከአምስት መቶ አንድ ለእግዚአብሔር ግብር ታወጣላችሁ።
ከእስራኤልም ልጆች ድርሻ እኩሌታ፥ ከሰዎችም፥ ከበሬዎችም፥ ከበጎችም፥ ከአህዮችም፥ ከእንስሶችም ሁሉ ከአምሳ አንድ ትወስዳለህ፤ የእግዚአብሔርንም ድንኳን ሥርዐት ለሚጠብቁ ለሌዋውያን ትሰጣለህ።”
እናንተም፥ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁም፥ ከእናንተ ጋር ክፍልና ርስት ስለሌለው በደጆቻችሁ ውስጥ የተቀመጠው ሌዋዊም በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ፊት ደስ ይበላችሁ።