እርስዋ በብላቴንነቷ ጊዜ በአባቷ ቤት ሳለች በአባትና በልጂቱ መካከል፥ ወይም በባልና በሚስት መካከል ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘው ሥርዐት ይህ ነው።
ዘኍል 31:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህኑም አልዓዛር ከሰልፍ የመጡትን ሰዎች አላቸው፥ “እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘው የሕጉ ሥርዐት ይህ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ካህኑ አልዓዛር ወደ ጦርነት ሄደው የነበሩትን ወታደሮች እንዲህ አላቸው፤ “እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው የሕጉ ሥርዐት ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካህኑም አልዓዛር ከጦርነት የተመለሱትን ወታደሮች እንዲህ አለ፦ “ጌታ ሙሴን ያዘዘው የሕጉ ሥርዓት ይህ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ አልዓዛር ከዘመቻ ለተመለሱት ወንዶች እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ለሙሴ የሰጠው የሕጉ ሥርዓት መመሪያዎች እነዚህ ናቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህኑም አልዓዛር ከሰልፍ የመጡትን ሰዎች አላቸው፦ እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘው የሕጉ ሥርዓት ይህ ነው፤ |
እርስዋ በብላቴንነቷ ጊዜ በአባቷ ቤት ሳለች በአባትና በልጂቱ መካከል፥ ወይም በባልና በሚስት መካከል ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ሙሴን ያዘዘው ሥርዐት ይህ ነው።