La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 16:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሙሴም ቆሬን አለው፥ “ማኅ​በ​ር​ህን ለይ፤ ነገ አንተ፥ ማኅ​በ​ር​ህም ሁሉ፥ አሮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዝግ​ጁ​ዎች ሁኑ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሙሴም ቆሬን እንዲህ አለው፤ “አንተና ተከታዮችህ እንዲሁም አሮን ነገ በእግዚአብሔር ፊት ትቀርባላችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሙሴም ቆሬን እንዲህ አለው፦ “ነገ አንተ፥ አንተንም የሚከተሉህ ሁሉ፥ አሮንም በጌታ ፊት ተገኙ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሙሴ ቆሬን እንዲህ አለው፦ “ነገ አንተና ሁለት መቶ ኀምሳ ተባባሪዎችህ ወደ እግዚአብሔር ድንኳን እንድትመጡ፤ አሮንም እዚያው ይገኛል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሙሴም ቆሬን፦ ነገ አንተ፥ ወገንህም ሁሉ፥ አሮንም በእግዚአብሔር ፊት ሁኑ፤

Ver Capítulo



ዘኍል 16:16
8 Referencias Cruzadas  

ሙሴም አሮ​ንን፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ፦ ‘ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁን ሰም​ቶ​አ​ልና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅረቡ’ በል” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወዲ​ያው ሙሴ​ንና አሮ​ንን ማር​ያ​ም​ንም፥ “ሦስ​ታ​ችሁ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ኑ ብሎ ተና​ገረ፤ ሦስ​ቱም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ወጡ።


ሙሴም እጅግ አዘነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አለው፥ “ወደ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው አት​መ​ል​ከት፤ እኔ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ችም ተመ​ኝቼ አል​ወ​ሰ​ድ​ሁም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው አል​በ​ደ​ል​ሁም።”


ሁላ​ች​ሁም ጥና​ዎ​ቻ​ች​ሁን ውሰዱ፤ ዕጣ​ንም አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ሁለት መቶ አምሳ ጥና​ዎ​ቻ​ች​ሁን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አምጡ፤ አንተ ደግሞ አሮ​ንም ጥና​ዎ​ቻ​ች​ሁን አምጡ” አለው።


ይህን አሳስባቸው፤ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፤ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና።


እነ​ሆኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና እርሱ በቀ​ባው ፊት መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ የማ​ንን በሬ ወሰ​ድሁ? የማ​ን​ንስ አህያ ወሰ​ድሁ? ማን​ንስ ሸነ​ገ​ልሁ? በማ​ንስ ላይ ግፍ አደ​ረ​ግሁ? ነጠላ ጫማ እን​ኳን ቢሆን ከማን እጅ መማ​ለጃ ተቀ​በ​ልሁ? መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ እኔ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”


አሁ​ንም ቁሙ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እፋ​ረ​ዳ​ች​ኋ​ለሁ፤ ለእ​ና​ን​ተና ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ ያደ​ረ​ገ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጽድቅ ሁሉ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።