ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድሩበትን ቦታ ታገኝላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ትቀድማቸው ነበር።
ዘኍል 14:44 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ ግን ተደፋፍረው ወደ ተራራው ራስ ወጡ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦትና ሙሴ ከሰፈሩ አልተንቀሳቀሱም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም ሆነ የእግዚአብሔር ታቦት ቃል ኪዳን ከሰፈር ሳይነሡ በስሜት ተገፋፍተው ብቻ ወደ ተራራማው አገር ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ቃል ኪዳን ታቦትና ሙሴ ከሰፈሩ ወጥተው ባይጓዙም እንኳ እነርሱ ግን ወደ ተራራው ራስ ለመውጣት ደፈሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ ግን ሌላው ቀርቶ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦትም ሆነ ሙሴ ከሰፈር ሳይነሡ ወደ ተራራማይቱ አገር ለመዝመት ደፍረው ተነሡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ ግን ወደ ተራራው ራስ ሊወጡ ደፈሩ፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦትና ሙሴ ከሰፈሩ አልተነሡም። |
ከእግዚአብሔርም ተራራ የሦስት ቀን መንገድ ያህል ተጓዙ፤ የእግዚአብሔርም የኪዳኑ ታቦት የሚያድሩበትን ቦታ ታገኝላቸው ዘንድ የሦስት ቀን መንገድ ትቀድማቸው ነበር።
ዐማሌቃዊና ከነዓናዊ በፊታችሁ ናቸውና በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ እግዚአብሔርን ከመከተል ተመልሳችኋልና እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር አይሆንም።”
የሀገር ልጅ ቢሆንም ወይም መጻተኛ ቢሆን፥ በእጁ ትዕቢትን የሚያደርግ ሰው እግዚአብሔርን ሰድቦአል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።
ሙሴም ከየነገዱ አንድ ሺህ ከሠራዊታቸውና ከካህኑ ከአሮን ልጅ ከአልዓዛር ልጅ ከፊንሐስ ጋር ሰደደ፤ ንዋያተ ቅድሳቱና ምልክት መስጫ መለከቶችም በእጆቻቸው ነበሩ።
እኔም ተናገርኋችሁ፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም፤ የእግዚአብሔርንም ቃል ተላለፋችሁ፤ በኀይላችሁም ወደ ተራራማው አገር ወጣችሁ።