La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 14:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ብ​ኝን እኒ​ህን ክፉ ማኅ​በር እስከ መቼ እታ​ገ​ሣ​ቸ​ዋ​ለሁ? ስለ እና​ንተ በእኔ ላይ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ትን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማጕ​ረ​ም​ረ​ምን ሰማሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ይህ ክፉ ማኅበረ ሰብ በእኔ ላይ የሚያጕረመርመው እስከ መቼ ነው? የእነዚህን ነጭናጮች እስራኤላውያን ማጕረምረም ሰምቻለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“የሚያጉረመርምብኝን ይህን ክፉ ማኅበር እስከ መቼ እታገሠዋለሁ? በእኔ ላይ የሚያጉረመርሙትን የእስራኤልን ልጆች ማጉረምረም ሰምቻለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እነዚህ ክፉዎች የሆኑ ሰዎች በእኔ ላይ የሚያጒረመርሙት እስከ መቼ ነው? እነዚህ አጒረምራሚዎች እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ሰምቻለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሚያጕረመርምብኝን ይህን ክፉ ሕዝብ እስከ መቼ እታገሠዋለሁ? በእኔ ላይ የሚያጕረመርሙትን የእስራኤልን ልጆች ማጕረምረም ሰማሁ።

Ver Capítulo



ዘኍል 14:27
11 Referencias Cruzadas  

“የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማን​ጐ​ራ​ጐር ሰማሁ፦ ማታ ሥጋን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ማለ​ዳም እን​ጀ​ራን ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ትእ​ዛ​ዞ​ች​ንና ሕጎ​ችን ለመ​ስ​ማት እስከ መቼ እንቢ ትላ​ላ​ችሁ?


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ክብር ጥዋት ታያ​ላ​ችሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ያን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁ​ትን ሰም​ቶ​አ​ልና፤ በእ​ኛም ላይ የም​ታ​ን​ጐ​ራ​ጕሩ እኛ ምን​ድን ነን?” አሉ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ፦ ‘ማን​ጐ​ራ​ጐ​ራ​ች​ሁን ሰም​ቶ​አ​ልና ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅረቡ’ በል” አለው።


አንተ አፍ​ህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደ​ረ​ግህ እኔ ሰም​ቼ​አ​ለሁ።”


ሕዝ​ቡም በክ​ፋት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አጕ​ረ​መ​ረሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በእ​ነ​ርሱ ላይ ነደ​ደች፤ ከሰ​ፈ​ሩም አን​ዱን ወገን በላች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “እኒህ ሕዝብ እስከ መቼ ያስ​ቈ​ጡ​ኛል? በፊ​ታ​ቸ​ውስ ባደ​ረ​ግ​ሁት ተአ​ም​ራት ሁሉ እስከ መቼ አያ​ም​ኑ​ብ​ኝም?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦


ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና “ተነሡ፤ አትፍሩም፤” አላቸው።


እርሱም መልሶ “የማታምን ትውልድ ሆይ! እስከመቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደ እኔ አምጡት፤” አላቸው።


ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዳ​ን​ዶቹ እን​ዳ​ን​ጐ​ራ​ጐ​ሩ​በት፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ትም እን​ደ​ጠፉ አና​ን​ጐ​ራ​ጕር።