ነህምያ 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀንደ መለከቱን ድምፅ ወደምትሰሙበት ስፍራ ወደዚያ ወደ እኛ ተሰብሰቡ፤ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል” አልኋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመለከት ድምፅ በምትሰሙበት ጊዜ፣ ወደ እኛ ተሰብሰቡ። አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእምቢልታ ድምፅ በምትሰሙበት ጊዜ ወደ እኔ መጥታችሁ በዙሪያዬ ተሰብሰቡ፤ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋልናል” አልኳቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀንደ መለከቱን ድምፅ ወደምትሰሙበት ስፍራ ወደዚያ ወደ እኛ ተሰብሰቡ፥ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል አልኋቸው። |
ታላላቆቹንና ሹሞቹን፥ የቀሩትንም ሕዝብ፥ “ሥራው ታላቅና ሰፊ ነው፤ እኛም በቅጥሩ ላይ ተበታትነናል፤ አንዱም ከሁለተኛው ርቆአል፤
የሰረገሎቹንም መንኰራኵር አሰረ፤ ወደ ጭንቅም አገባቸው፤ ግብፃውያንም፥ “እግዚአብሔር ስለ እነርሱ ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።
በፊታችሁ የሚሄደው አምላካችሁ እግዚአብሔር፥ በግብፅ ምድር እንዳደረገላችሁ ሁሉ፥ ስለ እናንተ አብሮአችሁ ይዋጋል፤