ደግሞ፥ “ቸር ነውና፥ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና” እያሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ እርስ በርሳቸው ያስተዛዝሉ ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቤት በተመሠረተ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያከበሩ በታላቅ ድምፅ ዘመሩ።
ነህምያ 12:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ ሁለቱ የአመስጋኞች ክፍሎች በእግዚአብሔር ቤት ቆሙ፤ ከእነርሱም ጋር እኔና የአለቆች እኩሌታ ነበርን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም ምስጋና ያቀረቡት ሁለቱ የመዘምራን ቡድኖች፣ በእግዚአብሔር ቤት ቦታቸውን ያዙ፤ እኔም ከግማሾቹ ሹማምት ጋራ ቦታዬን ያዝሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱ የምስጋና መዘምራን ክፍሎች በእግዚአብሔር ቤት ቆሙ፥ እኔና ከመሪዎቹ እኩሌታ በተጨማሪ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ሁኔታ የሁለቱም ቡድኖች ሰልፍ እግዚአብሔርን በመዝሙር በማመስገን ወደ ቤተ መቅደሱ ክልል ደረሰ፤ አብረውኝም ከነበሩት መሪዎች ጋር በተጨማሪ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ ሁለቱ የአመስጋኞች ተርታዎች በእግዚአብሔር ቤት ቆሙ፥ ከእነርሱም ጋር እኔና የአለቆች እኩሌታ፥ |
ደግሞ፥ “ቸር ነውና፥ ለእስራኤልም ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና” እያሉ እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እያከበሩ እርስ በርሳቸው ያስተዛዝሉ ነበር፤ የእግዚአብሔርም ቤት በተመሠረተ ጊዜ ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን እያከበሩ በታላቅ ድምፅ ዘመሩ።
ከኤፍሬምም በር በላይ፥ በአሮጌው በርና በዓሣ በር፥ በአናንኤልም ግንብ፥ በሃሜአ ግንብ እስከ በጎች በር ድረስ ሄዱ፤ በዘበኞችም በር አጠገብ ቆሙ።
ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ፥ ጐልማስነቴንም ደስ ወዳሰኛት ወደ አምላኬ እገባለሁ፤ አቤቱ፥ አምላኬ፥ በመሰንቆ አመሰግንሃለሁ።