ዳዊትም ሞዓባውያንን መታ፤ በምድርም ጥሎ በገመድ ሰፈራቸው፤ በሁለትም ገመድ ለሞት፥ በአንድም ገመድ ለሕይወት ሰፈራቸው፤ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት።
ሚክያስ 1:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ትሎት ለሞሬሼትጌት ትሰጪአለሽ፥ የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት አታላይ ይሆናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እናንተ ለሞሬሼትጌት፣ ማጫ ትሰጣላችሁ፤ የአክዚብ ከተማ፣ ለእስራኤል ነገሥታት መታለያ ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ለሞሬሼት ጋት የመሸኛ ስጦታዎችን ትሰጪአለሽ፤ የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት መታለያ ይሆናሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ሕዝብ ሆይ፥ እናንተ እንግዲህ ለሞሬሼት ጋት የመሰነባበቻ ስጦታ ትሰጣላችሁ፤ የአክዚብም ሕዝብ የእስራኤልን ነገሥታት ያታልላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ትሎት ለሞሬሼትጌት ትሰጪአለሽ፥ የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት አታላይ ይሆናሉ። |
ዳዊትም ሞዓባውያንን መታ፤ በምድርም ጥሎ በገመድ ሰፈራቸው፤ በሁለትም ገመድ ለሞት፥ በአንድም ገመድ ለሕይወት ሰፈራቸው፤ ሞዓባውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት።
አካዝም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሡ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ብርና ወርቅ ወስዶ ወደ አሦር ንጉሥ ገጸ በረከት አድርጎ ሰደደው።
ተባትና እንስት አንበሳ፥ እፉኝትም፥ ነዘር እባብም፥ በሚወጡባት በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል ብልጽግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሙአቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።
የሚያሳዝኑኝ በእኔ ላይ ለምን ይበረታሉ? ቍስሌስ ስለ ምን የማይፈወስ ሆነ? ስለ ምንስ አልሽርም አለ? እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃም ሆነብኝ።