Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሚክያስ 1:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ስለዚህ ለሞሬሼት ጋት የመሸኛ ስጦታዎችን ትሰጪአለሽ፤ የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት መታለያ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህ እናንተ ለሞሬሼትጌት፣ ማጫ ትሰጣላችሁ፤ የአክዚብ ከተማ፣ ለእስራኤል ነገሥታት መታለያ ትሆናለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 የይሁዳ ሕዝብ ሆይ፥ እናንተ እንግዲህ ለሞሬሼት ጋት የመሰነባበቻ ስጦታ ትሰጣላችሁ፤ የአክዚብም ሕዝብ የእስራኤልን ነገሥታት ያታልላሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ስለዚህ ትሎት ለሞሬሼትጌት ትሰጪአለሽ፥ የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት አታላይ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ስለዚህ ትሎት ለሞሬሼትጌት ትሰጪአለሽ፥ የአክዚብ ቤቶች ለእስራኤል ነገሥታት አታላይ ይሆናሉ።

Ver Capítulo Copiar




ሚክያስ 1:14
10 Referencias Cruzadas  

ቅዒላ፥ አክዚብ፥ መሪሳ፤ ዘጠኝ ከተሞችና መንደሮቻቸው።


ከዚህም በቀር አካዝ በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ሰብስቦ ለዚሁ ለአሦር ንጉሥ ገጸ በረከት በማድረግ ላከለት።


ለምን ሕመሜ የማያቋርጥ ሆነ? ቁስሌስ የማይፈወስ ለምን ሆነ? ለምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆንብኛለህን?


በደቡብ ስላሉ እንስሶች የተነገረ ራእይ። ተባትና እንስት፥ አንበሳ እፉኝትም፥ ተወርዋሪ እባብም በሚወጡባት፥ በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል፥ ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሟቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።


ሕዝቦች ሆይ፥ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ፥ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ፥ እግዚአብሔር መጠጊያችን ነው።


እንዲሁም ዳዊት ሞዓባውያንን ድል አደረገ፤ በመሬት ላይ አጋድሞ በገመድ ለካቸው፤ በገመድ ከተለኩትም ሁለት እጅ ሲገድል፥ አንድ እጅ ግን በሕይወት ይተው ነበር። ስለዚህ ሞዓባውያን የዳዊት ተገዢዎች ሆኑ፤ ገበሩለትም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios