ዘሌዋውያን 8:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህ ቀን እንደ ተደረገ ለእናንተ ለማስተስረያ ይደረግ ዘንድ እንዲሁ እግዚአብሔር አዘዘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዛሬ የተፈጸመው ይህ ሥርዐት ለእናንተ ማስተስረያ እግዚአብሔር ያዘዘው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዛሬ እንደተደረገው እንዲሁ ለእናንተ ማስተስረያም እንዲደረግ ጌታ አዝዞአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአታችሁን ለማስወገድ ይህን ዛሬ ያደረግነውን ሥርዓት እንድንፈጽም እግዚአብሔር አዞናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህ ቀን እንደ ተደረገ ለእናንተ ለማስተስረያ ይደረግ ዘንድ እንዲሁ እግዚአብሔር አዘዘ። |
እግዚአብሔር እንዲሁ አዝዞኛልና እንዳትሞቱ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ሌሊቱንና ቀኑን ሰባት ቀን ተቀመጡ፤ የእግዚአብሔርንም ሥርዐት ጠብቁ፤”
እርሱም እንደ እነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኀጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኀጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።