Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 7:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እር​ሱም እንደ እነ​ዚያ ሊቃነ ካህ​ናት አስ​ቀ​ድሞ ስለ ራሱ ኀጢ​አት በኋ​ላም ስለ ሕዝቡ ኀጢ​አት ዕለት ዕለት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሊያ​ቀ​ርብ አያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውም፤ ራሱን ባቀ​ረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድ​ር​ጎ​አ​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እርሱም እንደ ሌሎቹ ሊቃነ ካህናት መጀመሪያ ስለ ራሱ ኀጢአት፣ ከዚያም ስለ ሕዝቡ ኀጢአት በየቀኑ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ራሱን በሰጠ ጊዜ፣ ስለ ኀጢአታቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት አቅርቧልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 እርሱ እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት፥ አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት፥ ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ይህን ራሱን ባቀረበ ጊዜ አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እርሱ እንደ ሌሎቹ የካህናት አለቆች በመጀመሪያ ስለ ራሱ ኃጢአት፥ በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት በየቀኑ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ባቀረበ ጊዜ ይህን ነገር በማያዳግም ሁኔታ ፈጽሞታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 7:27
23 Referencias Cruzadas  

ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ለሚ​ቀ​ርቡ ከሳ​ዶቅ ዘር ለሚ​ሆኑ ለሌ​ዋ​ው​ያኑ ካህ​ናት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ከመ​ን​ጋው አንድ ወይ​ፈን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“አሮ​ንም ስለ ራሱ ኀጢ​አት የሚ​ሠ​ዋ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ኑን ያቀ​ር​ባል፤ ለራ​ሱም ለቤ​ተ​ሰ​ቡም ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ስለ ኀጢ​አቱ የእ​ር​ሱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈ​ኑን ያር​ዳል።


“ስለ ሕዝ​ቡም ኀጢ​አት የሚ​ሠ​ዋ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ፍየል ያር​ዳል፤ ደሙ​ንም ወደ መጋ​ረ​ጃው ውስጥ ያመ​ጣ​ዋል፤ በወ​ይ​ፈ​ኑም ደም እን​ዳ​ደ​ረገ በፍ​የሉ ደም ያደ​ር​ጋል፤ በመ​ክ​ደ​ኛው ላይና በመ​ክ​ደ​ኛው ፊት ይረ​ጨ​ዋል።


“አሮ​ንም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ወይ​ፈን ያቀ​ር​ባል፤ ለራ​ሱም፥ ለቤ​ተ​ሰ​ቡም ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል።


የሞተ አንድ ጊዜ ሞተ፤ በሞ​ቱም ኀጢ​አ​ትን ሻራት፤ የተ​ነ​ሣም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተነሣ።


እና​ንተ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ልት​ሆኑ በእ​ርሱ ታነ​ጻ​ችሁ።


ክር​ስ​ቶስ እንደ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ራሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ የሚ​ሆን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ቍር​ባን አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላ​ችሁ በፍ​ቅር ተመ​ላ​ለሱ።


መድኃኒታችንም ከዐመፅ ሁሉ እንዲቤዠን፥ መልካሙንም ለማድረግ የሚቀናውን ገንዘቡም የሚሆነውን ሕዝብ ለራሱ እንዲያነጻ፥ ስለ እኛ ነፍሱን ሰጥቶአል።


ሊቀ ካህ​ናት ሁሉ ስለ ኀጢ​አት መባ​ንና መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሊያ​ቀ​ርብ ከሰው ተመ​ርጦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሆ​ነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾ​ማ​ልና።


በዚ​ህም ምክ​ን​ያት ስለ ሕዝብ እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ርብ እን​ዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ስለ ኀጢ​አት ማቅ​ረብ ይገ​ባ​ዋል።


በም​ድር ቢሆን ኖሮ፥ ሊቀ ካህ​ናት ባል​ሆ​ነም ነበር፤ በኦ​ሪት ሕግ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​ቀ​ርቡ ካህ​ናት በእ​ር​ስዋ አሉና።


የዘ​ለ​ዓ​ለም መድ​ኀ​ኒ​ትን ገን​ዘብ አድ​ርጎ፥ በገዛ ደሙ አንድ ጊዜ ወደ መቅ​ደስ ገባ እንጂ በላ​ምና በፍ​የል ደም አይ​ደ​ለም።


ነውር የሌ​ለው ሆኖ፥ በዘ​ለ​ዓ​ለም መን​ፈስ ራሱን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረበ የክ​ር​ስ​ቶስ ደም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ከው ዘንድ ሕሊ​ና​ች​ንን ከሞት ሥራ እን​ዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?


ሊቀ ካህ​ናቱ ያደ​ር​ገው እንደ ነበረ፥ በያ​መ​ቱም ደም ይዞ ወደ ቅድ​ስት ይገባ እንደ ነበረ ዘወ​ትር ራሱን የሚ​ሠዋ አይ​ደ​ለም።


ይህስ ባይ​ሆን ዓለም ከተ​ፈ​ጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ በሞተ ነበር፤ አሁን ግን በዓ​ለም ፍጻሜ፥ ራሱን በመ​ሠ​ዋት ኀጢ​አ​ትን ይሽ​ራት ዘንድ አንድ ጊዜ ተገ​ለጠ።


እን​ዲሁ ክር​ስ​ቶ​ስም የብ​ዙ​ዎ​ችን ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድ​ና​ቸው ዘንድ ተስፋ ለሚ​ያ​ደ​ር​ጉት ያለ ኀጢ​አት ይገ​ለ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል።


ወደ ሁለ​ተ​ኛ​ዪቱ ክፍል ግን ሊቀ ካህ​ናቱ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ደም ይዞ፥ በየ​ዓ​መቱ አንድ ጊዜ ብቻ​ውን ይገባ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos