ዘሌዋውያን 6:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የአሮን ልጆች በእግዚአብሔር ፊት በመሠዊያው ፊት ለፊት የሚያቀርቡት የመሥዋዕት ሥርዐት ይህ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘የእህል ቍርባን ሥርዐት ይህ ነው፦ የአሮን ልጆች ቍርባኑን በመሠዊያው ትይዩ በእግዚአብሔር ፊት ያቅርቡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የእህሉም ቁርባን ሕግ ይህ ነው፤ የአሮን ልጆች በመሠዊያው ፊት ለፊት በጌታ ፊት ያቀርቡታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለ እህል መባ አቀራረብ የተደነገጉት መመሪያዎች እነዚህ ናቸው፦ ትውልዱ ከአሮን ዘር የሆነ ካህን የእህሉን መባ በመሠዊያው ፊት ለፊት ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእህሉም ቍርባን ሕግ ይህ ነው፤ የአሮን ልጆች በእግዚአብሔር ፊት በመሠዊያው ፊት ያቀርቡታል። |
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥቡታል። ካህኑም ሁሉን በመሠዊያው ላይ ለቍርባን ያቀርበዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው።
ከክንፎቹም ይሰብረዋል፤ ነገር ግን አይለየውም። ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ያኖረዋል፤ መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው።
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባሉ፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል።
ሙሴም አሮንን፥ የተረፉለትን ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን አላቸው፥ “ቅዱሰ ቅዱሳን ነውና ለእግዚአብሔር ከሆነው ከእሳት ቍርባን የቀረውን የስንዴውን ቍርባን ውሰዱ፤ ቂጣም አድርጋችሁ በመሠዊያው አጠገብ ብሉት፤
ካህኑም ከእህሉ ቍርባን መልካሙን የስንዴ ዱቄት ከዘይት ጋር እፍኝ ሙሉ፥ ደግሞም በእህሉ ቍርባን ላይ ያለውን ዕጣን ሁሉ ያነሣል፤ ለእግዚአብሔርም በጎ መዓዛ ያለው የመታሰቢያ ቍርባን እንዲሆን ለመታሰቢያ ነውና በመሠዊያው ላይ ይጨምረዋል።
ቍርባኑን ለእግዚአብሔር የሚያቀርብ የኢፍ መስፈሪያ አራተኛ እጅ በሆነ ዘይት የተለወሰ የኢፍ መስፈሪያ ዐሥረኛ እጅ የሆነ የመልካም ዱቄት መሥዋዕት ያመጣል።
ለአንዱም አውራ በግ የሚቃጠል ቍርባን ወይም መሥዋዕት ባደረጋችሁ ጊዜ የኢን መስፈሪያ ሢሶ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሁለት እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቍርባን ታዘጋጃላችሁ።
በላሙ ላይ የኢን መስፈሪያ ግማሽ በሆነ ዘይት የተለወሰ ከመስፈሪያው ከዐሥር እጅ ሦስት እጅ መልካም ዱቄት ለእህል ቍርባን ታቀርባለህ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ያን እንጀራ ከሰማይ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤ አባቴ ከሰማይ የእውነት እንጀራን ሰጥቶአችኋል እንጂ።