La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘሌዋውያን 6:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዘወ​ትር በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ እሳት ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በመሠዊያው ላይ ያለው እሳት ዘወትር ይንደድ፤ ምን ጊዜም አይጥፋ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይንደድ፤ እርሱም አይጥፋ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እሳቱም ሳይጠፋ በመሠዊያው ላይ ሁልጊዜ ይንደድ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዘወትር በመሠዊያው ላይ እሳት ይነድዳል፤ አይጠፋም።

Ver Capítulo



ዘሌዋውያን 6:13
9 Referencias Cruzadas  

“እኔ​ንም በክ​ህ​ነት እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉኝ ትቀ​ድ​ሳ​ቸው ዘንድ የም​ታ​ደ​ር​ግ​ላ​ቸው ነገር ይህ ነው፤ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን አንድ ወይ​ፈ​ንና ሁለት አውራ በጎች ትወ​ስ​ዳ​ለህ።


ቂጣ እን​ጀራ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወሰ የቂጣ እን​ጎቻ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ቀባ ስስ ቂጣ ከመ​ል​ካም ስንዴ ታደ​ር​ጋ​ለህ።


ከአ​ንዱ ጠቦ​ትም ጋር የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ በሆነ ተወ​ቅጦ በተ​ጠ​ለለ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ እጅ መል​ካም ዱቄት፥ ደግሞ ለመ​ጠጥ ቍር​ባን የኢን መስ​ፈ​ሪያ አራ​ተኛ እጅ የወ​ይን ጠጅ ታቀ​ር​ባ​ለህ።


ዓለ​ትም ትው​ጣ​ቸ​ዋ​ለች ድልም ይሆ​ናሉ የሸ​ሸም ይያ​ዛል። በጽ​ዮን ዘርእ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቤቶች ያሉት ብፁዕ ነው” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ወደ ሰሜ​ንም የሚ​መ​ለ​ከ​ተው ቤት መሠ​ዊ​ያ​ዉን ለማ​ገ​ል​ገል ለሚ​ተጉ ካህ​ናት ነው፤ እነ​ዚህ ከሌዊ ልጆች መካ​ከል ያገ​ለ​ግ​ሉት ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቀ​ርቡ የሳ​ዶቅ ልጆች ናቸው” አለኝ።


እሳ​ቱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ዘወ​ትር ይነ​ድ​ዳል፤ አይ​ጠ​ፋም፤ ካህ​ኑም ማለዳ ማለዳ ዕን​ጨት ያቃ​ጥ​ል​በ​ታል፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት በዚያ ላይ ይረ​በ​ር​ባል፤ በዚ​ያም የደ​ኅ​ን​ነ​ትን መሥ​ዋ​ዕት ስብ ያቃ​ጥ​ላል።


“የአ​ሮን ልጆች በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመ​ሠ​ዊ​ያው ፊት ለፊት የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት የመ​ሥ​ዋ​ዕት ሥር​ዐት ይህ ነው።


“አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ የሚ​ቃ​ጠ​ለው የመ​ሥ​ዋ​ዕቱ ሕግ ይህ ነው፤ የመ​ሠ​ዊ​ያው እሳት በላዩ እየ​ነ​ደ​ደች እስ​ኪ​ነጋ ትተ​ዉ​ታ​ላ​ችሁ።


እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ስቡ​ንም በላ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አይ​ተው ተደ​ነቁ፤ በግ​ም​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደቁ።