ዘሌዋውያን 16:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አሮንም ስለ ራሱ ኀጢአት የሚሠዋውን መሥዋዕት ወይፈኑን ያቀርባል፤ ለራሱም ለቤተሰቡም ያስተሰርያል፤ ስለ ኀጢአቱ የእርሱን መሥዋዕት ወይፈኑን ያርዳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሮን ለራሱና ለቤተ ሰቡ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ወይፈኑን የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ስለ ራሱ ያቅርብ፤ ወይፈኑንም ስለ ራሱ የኀጢአት መሥዋዕት አድርጎ ይረድ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አሮንም ለእርሱ የሆነውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈን ያቀርባል፤ ለራሱም ለቤተሰቡም ያስተሰርያል፤ ለእርሱ የሆነውን የኃጢአቱን መሥዋዕት ወይፈን ያርዳል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሮንም ኰርማውን ስለ ራሱና ስለ ቤተሰቡ የኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት በማድረግ ይረደው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም ስለ ራሱ ኃጢአት የሚሠዋውን መሥዋዕት ወይፈኑን ያቀርባል፤ ለራሱም ለቤተ ሰቡም ያስተሰርያል፤ ስለ ኃጢአቱ የእርሱን መሥዋዕት ወይፈኑን ያርዳል። |
ለቅድስተ ቅዱሳንም ያስተስርይ፤ ለምስክሩ ድንኳን፥ ለመሠዊያውም ያስተስርይ፤ ለካህናቱም፥ ለጉባኤውም ሕዝብ ሁሉ ያስተስርይ።
ሙሴም አሮንን፥ “ወደ መሠዊያው ቀርበህ የኀጢአትህን መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፤ ለራስህና ለወገንህ አስተስርይ፤ እግዚአብሔርም እንዳዘዘ የሕዝቡን ቍርባን አቅርብ፤ አስተስርይላቸውም” አለው።
እርሱም እንደ እነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኀጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኀጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።
ወደ ሁለተኛዪቱ ክፍል ግን ሊቀ ካህናቱ ኀጢአታቸውን ለማስተስረይ ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ የሚያቀርበውን ደም ይዞ፥ በየዓመቱ አንድ ጊዜ ብቻውን ይገባ ነበር።