Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 16:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከአ​ለው መሠ​ዊያ ላይ የእ​ሳት ፍም አም​ጥቶ ጥና​ውን ይሞ​ላል፤ ከተ​ወ​ቀ​ጠ​ውም ልቅ​ምና ደቃቅ ዕጣን እጁን ሙሉ ይወ​ስ​ዳል፤ ወደ መጋ​ረ​ጃ​ውም ውስጥ ያመ​ጣ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በእግዚአብሔር ፊት ካለው መሠዊያ ፍም ተወስዶ የተሞላበትን ጥና ይያዝ፤ ሁለት እጅ ሙሉ መልካም መዐዛ ያለው ዕጣን ይውሰድ፤ እነዚህንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ይዞ ይግባ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 በጌታም ፊት ካለው መሠዊያ ላይ ያለውን የእሳት ፍም በጥናው ሞልቶ ያመጣል፥ ከተወቀጠውም ከመዐዛው ያማረ ዕጣን በሁለቱ የእጁ መዳፎች ሙሉ ዘግኖ ይወስዳል፤ ወደ መጋረጃውም ውስጥ ያመጣዋል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከመሠዊያው የሚቃጠል የእሳት ፍም በጥናው ሞልቶም ሁለት እፍኝ ጣፋጭ ሽታ ያለውን የተወቀጠ ደቃቅ ዕጣን በመውሰድ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ያግባ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 በእግዚአብሔርም ፊት ካለው መሠዊያ ላይ የእሳት ፍም አምጥቶ ጥናውን ይሞላል፥ ከተወቀጠውም ከጣፋጭ ዕጣን እጁን ሙሉን ይወስዳል፤ ወደ መጋረጃውም ውስጥ ያመጣዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 16:12
13 Referencias Cruzadas  

የአ​ሮ​ንም ልጆች ናዳ​ብና አብ​ዩድ በየ​ራ​ሳ​ቸው ጥና​ውን ወስ​ደው እሳት አደ​ረ​ጉ​በት፤ በላ​ዩም ዕጣን ጨመ​ሩ​በት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያላ​ዘ​ዛ​ቸ​ውን ሌላ እሳት አቀ​ረቡ።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “ጥና​ህን ውሰድ፤ ከመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ እሳት አድ​ር​ግ​በት፤ ዕጣ​ንም ጨም​ር​በት፤ ወደ ማኅ​በ​ሩም ፈጥ​ነህ ውሰ​ደው፤ አስ​ተ​ስ​ር​ይ​ላ​ቸ​ውም፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቍጣ ወጥ​ቶ​አ​ልና፥ ሕዝ​ቡ​ንም ያጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ጀም​ሮ​አል” አለው።


እያ​ን​ዳ​ን​ዱም ጥና​ውን ወሰደ፤ እሳ​ትም አደ​ረ​ገ​በት፤ ዕጣ​ንም ጨመ​ረ​በት፤ ሙሴና አሮ​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ቆሙ።


የሚ​ቀ​ቡ​ትን የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት፥ ለመ​ቅ​ደሱ የሚ​ያ​ጥ​ኑ​ትን ዕጣን እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ ሁሉ ያድ​ርጉ።”


ነውር የሌ​ለው ሆኖ፥ በዘ​ለ​ዓ​ለም መን​ፈስ ራሱን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ረበ የክ​ር​ስ​ቶስ ደም ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ከው ዘንድ ሕሊ​ና​ች​ንን ከሞት ሥራ እን​ዴት ይልቅ ያነጻ ይሆን?


ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።


የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም የቅ​ብ​ዐ​ቱን ዘይት፥ ጥሩ​ው​ንም የጣ​ፋጭ ሽቱ ዕጣን በቀ​ማሚ ብል​ሃት እንደ ተሠራ አደ​ረገ።


ወደ ሁለ​ተ​ኛ​ዪቱ ክፍል ግን ሊቀ ካህ​ናቱ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ለማ​ስ​ተ​ስ​ረይ ስለ ራሱና ስለ ሕዝቡ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ደም ይዞ፥ በየ​ዓ​መቱ አንድ ጊዜ ብቻ​ውን ይገባ ነበር።


መልአኩም ጥናውን ይዞ የመሰዊያውን እሳት ሞላበት፤ ወደ ምድርም ጣለው፤ ነጐድጓድና ድምፅም መብረቅም መናወጥም ሆነ።


ፍር​ድ​ህን ለያ​ዕ​ቆብ፥ ሕግ​ህ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ያስ​ተ​ም​ራሉ፤ በማ​ዕ​ጠ​ን​ትህ ዕጣ​ንን፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ህም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሁል​ጊዜ ያቀ​ር​ባሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios