ዮሴፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታገሥ አልተቻለውም፥ “ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ” ብሎ ተናገረ፤ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አልነበረም።
መሳፍንት 3:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔግሎምም ከገልገል ከጣዖታቱ ቤት ተመለሰ። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብቻህ የምነግርህ የምሥጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግሎምም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ እንዲወጣ አዘዘ፤ በእርሱም ዘንድ የቆሙት ሁሉ ወጡ ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ራሱ ግን ጌልገላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፣ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩት አገልጋዮች በሙሉ ትተዉት ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ራሱ ግን ጌልጌላ አጠገብ ድንጋዮች ተጠርበው ከሚወጡበት አካባቢ ሲደርስ ወደ ኋላ በመመለስ ወደ ንጉሡ ሄዶ፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በምስጢር የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። ንጉሡም፥ “ጸጥታ” ሲል፤ አጠገቡ የነበሩትአገልጋዮች በሙሉ ትተውት ወጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤሁድ ራሱ ግን በጌልገላ አጠገብ ወዳሉት ተጠርበው ወደ ተተከሉ የጣዖት ድንጋዮች ዞር ብሎ ቈየ፤ ወደ ዔግሎንም ተመልሶ “ንጉሥ ሆይ! በግል ለአንተ የምነግርህ አንድ ምሥጢር አለኝ” አለው። እርሱም “ዝም በል” አለው። ስለዚህም ንጉሡ ባለሟሎቹን “እስቲ አንድ ጊዜ ውጪ ቈዩልን!” አላቸው፥ እነርሱም በሙሉ ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ናዖድ ግን በጌልገላ ከነበሩት ትክል ድንጋዮች ዘንድ ተመልሶ፦ ንጉሥ ሆይ፥ የምሥጢር ነገር አለኝ አለ፥ ንጉሡም፦ ዝም በል አለ፥ በዙሪያውም የቆሙት ሁሉ ወጡ። |
ዮሴፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታገሥ አልተቻለውም፥ “ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ” ብሎ ተናገረ፤ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አልነበረም።
ምጣዱንም ወስዳ በፊቱ ገለበጠች፤ እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አምኖንም፥ “ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስወጡ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ።
ናዖድም ወደ እርሱ ገባ፤ እርሱም በበጋ ቤቱ ሰገነት ለብቻው ተቀምጦ ነበር። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእግዚአብሔር መልእክት ለአንተ አለኝ” አለው። ዔግሎምም ከዙፋኑ ተነሣ፥ ቀረበውም።