ኢያሱ 21:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቄብጻይምንና መሰማርያዋን፥ ቤቶሮንና መሰማርያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቂብጻይሞና ቤትሖሮን ከነመሰማሪያዎቻቸው አራት ከተሞች ተሰጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቂብጻይምንና መሰማሪያዋን፥ ቤት-ሖሮንንና መሰማሪያዋን፤ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቂብጻይምና ቤትሖሮን የተባሉት ከግጦሽ መሬቶቻቸው ጋር ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቂብጻይምንና መሰምርያዋን፥ ቤትሖሮንንና መሰምርያዋን፥ አራቱን ከተሞች ሰጡአቸው። |
ወደ ምዕራብም እስከ የፍሌጣውያን ዳርቻ እስከ ታችኛው ቤቶሮን ዳርቻ ድረስ ይወርዳል፤ መውጫውም በባሕሩ አጠገብ ነበረ።
የኤፍሬምም ልጆች ድንበር በየወገኖቻቸው እንደዚህ ነበረ፤ የርስታቸው ድንበር ከአጣሮትና፥ ከኤሮሕ ምሥራቅ ከጋዛራ እስከ ላይኛው ቤቶሮን ድረስ ነበረ፤