ዮሐንስ 8:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ቃሌን ለምን አታስተውሉም? ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምናገረውን ለምን አታስተውሉም? ምክንያቱም ቃሌን መስማት ስለማትችሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድነው? ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ምን ንግግሬ አይገባችሁም? ንግግሬን ለመስማት ስለማትችሉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንግግሬን የማታስተውሉ ስለ ምንድር ነው? ቃሌን ልትሰሙ ስለማትችሉ ነው። |
እርሱም፥ “ሂድ፤ ይህን ሕዝብ፦ መስማትን ትሰማላችሁ፥ አታስተውሉምም፤ ማየትንም ታያላችሁ፥ አትመለከቱምም” በላቸው አለኝ።
ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ? ለማንስ አዳኛለሁ? እነሆ፥ ጆሮአቸው ያልተገረዘች ናት፤ ለመስማትም አይችሉም፤ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል፥ ይሰሙት ዘንድ አልፈቀዱምና።
ከእንግዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤፍሬም ምንድን ነው? እኔ አደከምሁት፤ አጸናሁትም፤ እኔ እንደ ተወደደ አበባ አፈራዋለሁ፤ ፍሬህም በእኔ ዘንድ ይገኛል።
በዐይናቸው እንዳያዩ፥ በጆሮአቸውም እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም እንዳያስተውሉ፥ ተመልሰውም እንዳልፈውሳቸው፥ የዚህ ሕዝብ ልብ ደንድኖአልና ጆሮአቸውም ደንቁሮአል ዐይናቸውንም ጨፍነዋል፤’ የሚል የኢሳይያስ ትንቢት በእነርሱ ይፈጸማል።
“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ቃል የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም ይድናሉ።
ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድድ ግን ትምህርቴ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ሆነች፥ የምናገረውም ከራሴ እንዳይደለ እርሱ ያውቃል።
እነርሱም መልሰው፥ “እኛ የአብርሃም ዘር ነን፤ ከሆነ ጀምሮ ለማንም ከቶ ባሮች አልሆንም፤ እንግዲህ እንዴት አርነት ትወጣላችሁ ትለናለህ?” አሉት።
እነርሱም መልሰው፥ “የእኛስ አባታችን አብርሃም ነው” አሉት፤ ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የአብርሃም ልጆች ብትሆኑስ የአብርሃምን ሥራ በሠራችሁ ነበር።
“እናንተ አንገታችሁ የደነደነ፥ ልባችሁም የተደፈነ፥ ጆሮአችሁም የደነቈረ፥ እንደ አባቶቻችሁ መንፈስ ቅዱስን ዘወትር ትቃወማላችሁ።