በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።
ዮሐንስ 7:48 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአለቆች ወይም ከፈሪሳውያን ያመነበት አለን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ ከባለሥልጣኖችና ከፈሪሳውያን በርሱ ያመነ አለ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአለቆች ወይም ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመነ አለን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለመሆኑ ከባለ ሥልጣኖች ወይም ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመኑ አሉን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከአለቆች ወይስ ከፈሪሳውያን በእርሱ ያመነ አለን? |
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “አባት ሆይ! የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።
ከሕዝቡ አለቆችም ያመኑበት ብዙዎች ነበሩ፤ ነገር ግን ከምኵራብ አስወጥተው እንዳይሰዱአቸው በፈሪሳውያን ምክንያት አልመሰከሩለትም።
እነሆ፥ እርሱ በገሀድ ይናገራል፤ እነርሱ ግን ምንም የሚሉት የለም፤ ይህ በእውነት ክርስቶስ እንደ ሆነ ምናልባት አለቆች ዐውቀው ይሆን?
የእግዚአብሔርም ቃል ከፍ ከፍ አለ፤ በኢየሩሳሌምም ምእመናን እጅግ በዙ፤ ከካህናትም መካከል ያመኑ ብዙዎች ነበሩ።
እንግዲህ ጥበበኛ ማን ነው? ጸሓፊስ ማን ነው? ይህን ዓለምስ የሚመረምረው ማን ነው? እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ጥበብ ስንፍና አላደረገውምን?