እግዚአብሔርም ከሰውነቱ ሕማምን ያርቅ ዘንድ ይወዳል፤ ብርሃንንም ያሳየዋል፤ በጥበቡም ይለየዋል፤ ለጽድቅና ለበጎ ነገር የሚገዛውን ጻድቁን ያጸድቀዋል። የብዙዎችንም ኀጢአታቸውን እርሱ ይደመስሳል።
ዮሐንስ 15:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደስታዬ በእናንተ ይኖር ዘንድ፥ ደስታችሁም ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን ነገርኋችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደስታዬ በእናንተ እንዲሆንና ደስታችሁም ሙሉ እንዲሆን ይህን ነግሬአችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደስታዬም በእናንተ እንዲሆን፥ ደስታችሁም ፍጹም እንዲሆን ይህን ነግሬአችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን የነገርኳችሁ ደስታዬ በእናንተ እንዲሆንና የእናንተም ደስታ ፍጹም እንዲሆን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደስታዬም በእናንተ እንዲሆን ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን ነግሬአችኋለሁ። |
እግዚአብሔርም ከሰውነቱ ሕማምን ያርቅ ዘንድ ይወዳል፤ ብርሃንንም ያሳየዋል፤ በጥበቡም ይለየዋል፤ ለጽድቅና ለበጎ ነገር የሚገዛውን ጻድቁን ያጸድቀዋል። የብዙዎችንም ኀጢአታቸውን እርሱ ይደመስሳል።
ከእንግዲህ ወዲህ፥ “የተተወች” አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፥ “ውድማ” አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፥ “ደስታዬ የሚኖርባት” ትባያለሽ፤ ምድርሽም፥ “ባል ያገባች” ትባላለች።
ለእነርሱም መልካምን በማድረግ ይቅር እላቸዋለሁ፤ በእውነትም በፍጹም ልቤና በፍጹም ነፍሴ በዚህች ምድር እተክላቸዋለሁ።
ይህችም ከተማ እኔ የምሠራላቸውን በጎነት ሁሉ በሚሰሙ፥ እኔም ስላመጣሁላቸው በጎነትና ሰላም ሁሉ በሚፈሩና በሚደነግጡ አሕዛብ ሁሉ ፊት ለደስታ፥ ለክብርና ለገናንነት ትሆናለች።”
አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው፣ በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፥ በፍቅሩም ያርፋል፥ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል ይባላል።
ነገር ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ሆኖአልና፥ ጠፍቶም ተገኝቶአልና፥ ደስ ሊለን፥ ሐሤትም ልናደርግ ይገባል።”
ያገኘቻት እንደ ሆነም ወዳጆችዋንና ጎረቤቶችዋን ጠርታ፦ ‘የጠፋችኝን ድሪሜን አግኝቼአታለሁና፥ ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ’ ትላቸዋለች።
በእኔም ሰላምን እንድታገኙ ይህን ነገርኋችሁ፤ በዓለም ግን መከራን ትቀበላላችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለሙን ድል ነሥቼዋለሁና።”
ሙሽራ ያለችው ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው የሙሽራው ሚዜ ግን በሙሽራው ቃል እጅግ ደስ ይለዋል፤ የእኔ ደስታ አሁን ተፈጸመች።
የተስፋ አምላክ እግዚአብሔርም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል በተስፋ ያበዛችሁ ዘንድ በእምነት ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይፈጽምላችሁ።
ደስ የሚላችሁን እንድታደርጉ እንረዳችኋለን እንጂ እንድታምኑ ግድ የምንላችሁ አይደለም፤ በእምነት ቆማችኋልና።
እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።
እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልወድም፤ ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍም ልናገራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።