ኢዮብ 9:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በዐውሎ ነፋስ ይቀጠቅጠኛል፤ ያለ ምክንያት ብዙ ጊዜ ያቈስለኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፤ ቍስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፥ ቁስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዐውሎ ነፋስ ያደቀኛል ያለ ምክንያትም ቊስሌን ያበዛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፥ ቍስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛል። |
ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊትም በአጠገቡ ተቀመጡ፤ ሕማሙ እጅግ አስፈሪና ታላቅ እንደ ነበረ አይተዋልና ከእነርሱ አንድ ቃል የሚናገረው አልነበረም።
እግዚአብሔርም ሰይጣንን አለው፥ “በባሪያዬ በኢዮብ ላይ እንዲህ እንዳታስብ ተጠንቀቅ፤ በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ ገር፥ ጻድቅና ንጹሕ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ከክፋትም ሁሉ የራቀ፥ ዳግመኛም ቅን የሆነ ሰው የለምና፤ አንተ ግን ሀብቱን በከንቱ አጠፋ ዘንድ ነገርኸኝ።”
ፍርዴን ለተስፋ ይቅርታዬንም ለትክክለኛ ሚዛን አደርጋለሁ፤ በከንቱና በሐሰት የሚታመኑ ከዐውሎ ነፋስ አያመልጡም።
እነሆ ከእግዚአብሔር ዘንድ ንውጽውጽታ ይመጣል፤ ኃጥኣንን ያነዋውጣቸውና ይገለብጣቸው ዘንድ መቅሠፍት ይመጣባቸዋል፤ የዐመፀኞችን ራስ ይገለባብጣል።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመዓቴ በዐውሎ ነፋስ እሰነጣጥቀዋለሁ፤ ያጠፋውም ዘንድ በቍጣዬ የሚያሰጥም ዝናብ፥ በመዓቴም ታላቅ የበረዶ ድንጋይ አወርዳለሁ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፥ “የእግዚአብሔር ሥራ ሊገለጥበት ነው እንጂ እርሱ አልበደለም፤ ወላጆቹም አልበደሉም።