ኢዮብ 38:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማንም በሌለበት ምድር ላይ፥ ሰውም በማይኖርበት ምድረ በዳ ይዘንም ዘንድ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህም ማንም የማይኖርበትን ምድር፣ ሰውም የሌለበትን ምድረ በዳ የሚያጠጣ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ማንም በሌለበት ምድር፥ ሰው በማይኖርበት ምድረ በዳ፥ |
በላይ በሰማይ ውኆችን ይሰበስባል፤ ከምድርም ዳርቻ ደመናትን ከፍ ያደርጋል፤ ለዝናብም መብረቅን ያደርጋል፤ ነፋስንም ከቤተ መዛግብቱ ያወጣል።
በውኑ በአሕዛብ ጣዖታት መካከል ያዘንብ ዘንድ የሚችል ይገኛልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ሊሰጥና ሊያጠግብ ይችላልን? አቤቱ አምላካችን ሆይ አንተ አይደለህምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድርገሃልና ስለዚህ አንተን በተስፋ እንጠባበቃለን።