ከብቶቻቸውንም ወደ ዮሴፍ አመጡ፤ ዮሴፍም በፈረሶቻቸው፥ በበጎቻቸውም፥ በላሞቻቸውም፥ በአህዮቻቸውም ፈንታ እህልን ሰጣቸው፤ በዚያች ዓመትም ስለ ከብቶቻቸው ሁሉ ፈንታ እህልን መገባቸው።
ኢዮብ 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰይጣንም መልሶ ለእግዚአብሔር፥ “ቍርበት ስለ ቍርበት ነው፤ ሰው ያለውን ሁሉ ስለ ሕይወቱ ይሰጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰይጣንም እንዲህ ሲል ለእግዚአብሔር መለሰ፤ “ ‘ቍርበት ስለ ቍርበት ነው’ እንዲሉ ሰው ለሕይወቱ ሲል ያለውን ሁሉ ይሰጣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰይጣንም መልሶ ጌታን እንዲህ አለው፦ “በቆዳ ላይ ቆዳ፥ ሰው ያለውን ሁሉ ስለ ሕይወቱ ይሰጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰይጣንም “በቊርበት ፈንታ ቊርበት” እንዲሉ፥ “ሰው እኮ ሕይወቱን ለማትረፍ ሲል ያለውን ሁሉ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰይጣንም መልሶ እግዚአብሔርን፦ ቁርበት ስለ ቁርበት ነው፥ ሰው ያለውን ሁሉ ስለ ሕይወቱ ይሰጣል። |
ከብቶቻቸውንም ወደ ዮሴፍ አመጡ፤ ዮሴፍም በፈረሶቻቸው፥ በበጎቻቸውም፥ በላሞቻቸውም፥ በአህዮቻቸውም ፈንታ እህልን ሰጣቸው፤ በዚያች ዓመትም ስለ ከብቶቻቸው ሁሉ ፈንታ እህልን መገባቸው።
እንግዲህ እኛ በፊትህ እንዳንሞት፥ ምድራችንም እንዳትጠፋ፥ እኛንም፥ ምድራችንንም በእህል ግዛን፤ እኛም ለፈርዖን አገልጋዮች እንሁን፤ ምድራችንም ለእርሱ ትሁን፤ እኛ እንድንድን፥ እንዳንሞትም፥ ምድራችንም እንዳትጠፋ እንዘራ ዘንድ ዘር ስጠን።”
እግዚአብሔርም ሰይጣንን አለው፥ “በባሪያዬ በኢዮብ ላይ እንዲህ እንዳታስብ ተጠንቀቅ፤ በምድር ላይ እንደ እርሱ ያለ ገር፥ ጻድቅና ንጹሕ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ከክፋትም ሁሉ የራቀ፥ ዳግመኛም ቅን የሆነ ሰው የለምና፤ አንተ ግን ሀብቱን በከንቱ አጠፋ ዘንድ ነገርኸኝ።”
በዚያም የተገኙ ዐሥር ሰዎች ቀርበው እስማኤልን እንዲህ አሉት፥ “በሜዳው ድልብ አለንና፥ ገብስና ስንዴ፥ ዘይትና ማርም አለንና አትግደለን፤” እርሱም በወንድሞቻቸው መካከል እነርሱን መግደል ተወ።
“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
መልሰውም ኢያሱን፥ “እኛ ባሪያዎችህ ምድሪቱን ሁሉ ይሰጣችሁ ዘንድ፥ በእርስዋም የሚኖሩትን ሁሉ ከፊታችሁ ያጠፋ ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር ባሪያውን ሙሴን እንዳዘዘ በእውነት ሰምተናል፤ ስለዚህም ከእናንተ የተነሣ ስለ ነፍሳችን እጅግ ፈራን፤ ይህንም ነገር አድርገናል፤